ንብ በሚያረባ ሰው ላይ የተደረገ ተአምር

ብዙ ንብ ያለው ሰው ነበር፡፡ ከሰው ሁሉ ይልቅ ፈጽሞ ንቡ ይበዛለት ዘንድ ይወድ ነበር፡፡ ወደ አንዲት ሥርየኛ ሴት ሒዶ ንቤ ይበዛልኝ ዘንድ መዓርም ሰምም ከሰው ሁሉ ይልቅ ይበዛልኝ ዘንድ የምሠራውን ሥራ እንትመክሪኝ እለምንሻለሁ አላት፡፡ ያችም ሥራየኛ ሴት እኔስ ሥጋውን ደሙን በተቀበልህ ጊዜ ካፍህ አውጥተህ በዚያ ቀፎ ውስጥ ጨምረው ብዙ ንብ ሰምና ማርም ይሆንልሀል ብየ እመክርሀለሁ አለችው፡፡ በሁለተኛውም ቀን ወደ ቤተክርስቲያን ሒዶ ሥጋውን ደሙን ተቀብሎ እን ነገረች አደረገና ካፉ አውጥቶ በንቡ ውስጥ ጨምሮ አንዲት ሰዓት እልፍ አለ፡፡ ሁለተኛም ንብ ወዳለበት በተመለሰ ጊዜ ሥጋውን ካስቀመጠበት ከዚያ ቀፎ ውስጥ እጅግ ፍጹም ብርሃንና የእመቤታችን ሥዕል በዚያ ቀፎ ውስጥ በንቦች መካከል ተቀምጦ አየ፡፡ በደረቷም ከፀሐይና … Continue reading ንብ በሚያረባ ሰው ላይ የተደረገ ተአምር