ውድ የዚህ ድረ ገጽ ተከታታዮች እንኳን ለደስተኛይቱ ክብርት ስለሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም የሥጋዋ ፍለሰት በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ለዛሬ ከቤተ ክርስቲያናችን እንደ ጠፈር ሰፊና እንደ ውቅያኖስ ጥልቅ ከሆነው የእመቤታቸን ነገረ ሕይወቷንና ተአምራቷን ከሚገልጡት ሥዕሎች መካከል ተወዳጅ የሆነውን የፍልሰታዋ ሥዕልን አጭር መግለጫ ከአሣሣሉ ጋር አቅርቤያለሁ፡፡ መልካም ንባብ የእመቤታችን ፍቅሯ ጠዓሟ እና አማላጅነቷ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማታያስ እና ሌሎች ብፁዓን ጳጳሳት አባቶቻችንና ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር ይኑር፡፡ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሥዕሎች ምንጫቸው መጽሐፍ ቅዱስና አዋልድ መጻሕፍት ሲሆን፤ በእነዚህ መጻሕፍት ውስጥ የተገለጠው እውነትም በጊዜ እና በቦታ ሳይወሰን ቅዱሳት ሥዕሎች ይሣላሉ፡፡ ከእነዚህ ሥዕሎች መካከልም የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሰተ ሥጋዋ ሥዕል አንዱ ነው፡፡ ለዚህ ሥዕል መነሻ … Continue reading ሥዕለ ፍልሰታ ለማርያም