የደብረ ዘመዶዋ ‹‹ግብጻዊት›› ሥዕለ ማርያምና ተአምራት ክፍል 1

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሉቃስ ሥዕል ተብለው የሚጠሩ ሥዕሎች የሚገኙባቸው ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት መካከል <<ደብረ ዘመዶ>> አንዷ ስትሆን በዚህች ቤተ ክርስቲያን የምትገኘው ሥዕልም ግብጻዊት … Continue reading የደብረ ዘመዶዋ ‹‹ግብጻዊት›› ሥዕለ ማርያምና ተአምራት ክፍል 1

ሥዕለ ቅዱስ ደቅስዮስ

አዘጋጅ፡- ኃይለማርያም ሽመልስ facebook.com/ethioicons  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በታህሳስ 22 ከሚዘከሩት ቅዱሳን መካከል ቅዱስ ደቅስዮስ ሲሆን ይህ ቅዱስ አባት የእመቤታችንን ተአምር ከፍቅሯ የተነሣ አሰባስቦ ያዘጋጀ አባት ነው፡፡ … Continue reading ሥዕለ ቅዱስ ደቅስዮስ

ሥዕለ ፍልሰታ ለማርያም

ውድ የዚህ ድረ ገጽ ተከታታዮች እንኳን ለደስተኛይቱ ክብርት ስለሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም የሥጋዋ ፍለሰት በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ለዛሬ ከቤተ ክርስቲያናችን እንደ ጠፈር ሰፊና እንደ ውቅያኖስ ጥልቅ ከሆነው የእመቤታቸን ነገረ ሕይወቷንና ተአምራቷን ከሚገልጡት ሥዕሎች መካከል ተወዳጅ የሆነውን የፍልሰታዋ ሥዕልን አጭር መግለጫ ከአሣሣሉ ጋር አቅርቤያለሁ፡፡ መልካም ንባብ የእመቤታችን ፍቅሯ ጠዓሟ እና አማላጅነቷ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማታያስ እና ሌሎች ብፁዓን ጳጳሳት አባቶቻችንና ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር ይኑር፡፡ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሥዕሎች ምንጫቸው መጽሐፍ ቅዱስና አዋልድ መጻሕፍት ሲሆን፤ በእነዚህ መጻሕፍት ውስጥ የተገለጠው እውነትም በጊዜ እና በቦታ ሳይወሰን ቅዱሳት ሥዕሎች ይሣላሉ፡፡ ከእነዚህ ሥዕሎች መካከልም የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሰተ ሥጋዋ ሥዕል አንዱ ነው፡፡ ለዚህ ሥዕል መነሻ … Continue reading ሥዕለ ፍልሰታ ለማርያም

አባ ጽጌ ድንግል ስለ እመቤታችን ሥዕል ከተናገሩት

‹‹የአበባ ወራት ባለፈ ጊዜ ምስጋናሽን ሳመሰግን በሥዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም፣ ስምሽን መጥራት የወደቀውን ያነሣል ኃጥኡንም ጻድቅ ያደርጋልና፡፡›› Continue reading አባ ጽጌ ድንግል ስለ እመቤታችን ሥዕል ከተናገሩት

ሥዕለ ልደታ ለማርያም

‹‹ልደታ›› በመባል በተለምዶ በማሳጠር የሚጠራው እና ወር በገባ በአንደኛው ቀን የሚከበረው የወላዲተ አምላክ የቅድስት ድንግል ማርያም ከቅዱስ ኢያቄምና ከቅድስት ሐና በሊባኖስ ተራራ በግንቦት አንድ ቀን የተወለደችበትን … Continue reading ሥዕለ ልደታ ለማርያም

ንብ በሚያረባ ሰው ላይ የተደረገ ተአምር

ብዙ ንብ ያለው ሰው ነበር፡፡ ከሰው ሁሉ ይልቅ ፈጽሞ ንቡ ይበዛለት ዘንድ ይወድ ነበር፡፡ ወደ አንዲት ሥርየኛ ሴት ሒዶ ንቤ ይበዛልኝ ዘንድ መዓርም ሰምም ከሰው ሁሉ ይልቅ ይበዛልኝ ዘንድ የምሠራውን ሥራ እንትመክሪኝ እለምንሻለሁ አላት፡፡ ያችም ሥራየኛ ሴት እኔስ ሥጋውን ደሙን በተቀበልህ ጊዜ ካፍህ አውጥተህ በዚያ ቀፎ ውስጥ ጨምረው ብዙ ንብ ሰምና ማርም ይሆንልሀል ብየ እመክርሀለሁ አለችው፡፡ በሁለተኛውም ቀን ወደ ቤተክርስቲያን ሒዶ ሥጋውን ደሙን ተቀብሎ እን ነገረች አደረገና ካፉ አውጥቶ በንቡ ውስጥ ጨምሮ አንዲት ሰዓት እልፍ አለ፡፡ ሁለተኛም ንብ ወዳለበት በተመለሰ ጊዜ ሥጋውን ካስቀመጠበት ከዚያ ቀፎ ውስጥ እጅግ ፍጹም ብርሃንና የእመቤታችን ሥዕል በዚያ ቀፎ ውስጥ በንቦች መካከል ተቀምጦ አየ፡፡ በደረቷም ከፀሐይና … Continue reading ንብ በሚያረባ ሰው ላይ የተደረገ ተአምር

መግቢያ ጠባቂዋ ሥዕለ ማርያም፡ PANAGIA PORTAITISSA

መግቢያ ጠባቂዋ ‹‹Panagia Portaitissa›› በመባል የምትታወቀውና ቅዱስ ሉቃስ ሣላቸው ከሚባሉ ቅዱሳት የእመቤታችን ሥዕላት መካከል ስትሆን በምስራቁ የባይዛነቲን ክርስቲያን ሀገር በየካቲት 4 በዓሏ የሚታሰብላት የእመቤታችን ሥዕል ናት፡፡ … Continue reading መግቢያ ጠባቂዋ ሥዕለ ማርያም፡ PANAGIA PORTAITISSA

ሥዕለ በዓታ ለማርያም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምለክ አሜን፡፡ ውድ ኦርቶዶክሳውያን የወላዲተ አምላክ የአሥራት ልጆች እንኳን ለእናታችን እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ፡፡ በጸሎት … Continue reading ሥዕለ በዓታ ለማርያም

ኅዳር 21: የቅድስት ድንግል ማርያም እና የታቦተ ጽዮን በዓል

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፡፡ በዛሬው እለት ከማኅበራዊ ድረገጽ ያገኘሁትን ታቦተ ጽዮን ታላቅ ተአምራትን በዳጎን ላይ ማድረጓን የሚገልጸውን ሥዕል ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በፎቶ የተነሣ ሥዕል በማግኘቴ ላካፍላችሁ በማለት ይህችን ጽሑፍ ጽፌያለሁ፡፡ በቀጣይ ዕትም የእመቤታችን ቅድስት … Continue reading ኅዳር 21: የቅድስት ድንግል ማርያም እና የታቦተ ጽዮን በዓል

ሥዕለ ኪዳነ ምሕረት

ኦርቶዶክሳውያን እንደ እግዚአብሔር ቸርነትና እና ቅዱሳን አማላጅነት መጠን በዚህ ጦማር በየቀኑ በዚህ የቅዱሳን ነቢያት ጾም ወቅት ልዩ ልዩ የሆኑ የቅዱሳን ሥዕላትን ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡ እንዲቀርብ የምትፈልጉት የቅዱስ … Continue reading ሥዕለ ኪዳነ ምሕረት