ሥዕለ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀመላእክት


አዘጋጅ ኃይለማርያም ሽመልስ /በቅዱሳት ሥዕላት ዙርያ ጥናት አጥኚ እና ሠዓሊ/


ይህ ሥዕል ተሣለው በ18ኛው መ.ክ.ዘ. ሲሆን፤ በተለምዶ የአሣሣል ዘይቤው ሁለተኛው የጎንደር ዘይቤ በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህ ሥዕል ላይ የምንመለከተው ሊቀ መላእኩ ቅዱስ ሚካኤል በክብር ተቀምጦ እና በሠራዊተ መላእክት ዘንድ ተሸሞ ነው፡፡ ይህ ሥዕል ላይ ሹመቱ በቅዱሳን መላእክት ዘንድ ብቻ ሳይሆን በዲያቢሎስ እና በሠራዊቶቹ መሆኑን ለማጠየቅ ሰይጣን በሰንሰለት ተይዞ እንዲሁም በእሳት ውስጥ እየተቃጠለ ከሥዕሉ የታችኛው ክፍል ላይ ተሥሏል፡፡

የቅዱስ ሚካኤል ክብሩንና በጸጋ እግዚአብሔር የተመላ መሆኑን ለመግለጽም አለባበሱም ብዙ ጌጥ እና የተዝረፈረፈ ሲደረግ ሰይጣን በዚህ ተቃራኒ ልብስ ሳይለብስ እርቃኑን ሆኖ ተሥሏል፡፡ የዚህ ምሳሌነቱም ከጸጋ እግዚአብሔር መራቆቱን ለመግለጽ ሲሆን ከቅዱስ ሚካኤል በታች እና የተዋረደ መሆኑን ለማጠየቅም የሥዕሉ ታችኛውን ክፍል ላይ ተሥሎ ይገኛል፡፡

ስለ ቅዱሳት ሥዕላት ምስጢር እና ምሳሌ ማወቅ ለምትሹ ‹‹ኦርቶዶኮሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት፡EthioIcons›› ድረ ገጽ ይከታተሉ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ ይቀላቀሉ፡፡


ምንጭ፡

www.bl.uk/manuscripts/FullDisplay.aspx?index=96&ref=Or_615

ኃይለማርያም ሽመልስ: ጥቅምት 2012 © ‹‹ኦርቶዶኮሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት፡EthioIcons››

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s