የደብረ ዘመዶዋ ‹‹ግብጻዊት›› ሥዕለ ማርያምና ተአምራት ክፍል 1


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሉቃስ ሥዕል ተብለው የሚጠሩ ሥዕሎች የሚገኙባቸው ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት መካከል <<ደብረ ዘመዶ>> አንዷ ስትሆን በዚህች ቤተ ክርስቲያን የምትገኘው ሥዕልም ግብጻዊት በመባል ትታወቃለች፡፡

ይህች ሥዕልም በትውፊት ዓፄ ናዖድ የአቡነ ዮሐንስ ወዳጅ ስለነበሩ ሥዕለ ማርያምን አምጥተዉ  ለአቡነ ዮሐንስ ቢሰጧዋቸው አቡነ ዮሐንስ የእመቤታችንን ቤተ መቅደስ በሚሰሩበት ቤተ መቅደሱ ተሰርቶ እንደተጠናቀቀ ሥዕለ ሉቃስ በዚያ አስቀምጠዋታል፡፡ ከሥር ግብጻዊት ማርያም የፈጸመችውን ተአምር አንዱን እነሆ፡-

አቡነ ዮሐንስ ካረፉ በኋላ በአካባቢዉ አንድ ሰዉ ዘወትር ጠዋት ማታ እየመጣ ከሥዕሏ ፊት ያለቅስ ነበር፡፡ ሥዕለ ማርያምም አትቆፍር አታርስ ዘወትር ከፊቴ እየመጣህ ታለቅሳለህ፡፡ ምን ሆነህ ነዉ ምንስ ላድርግልህ በማለት ጠየቀችዉ፡፡ ሰዉየዉም መልስ ሳይሰጣት እየተመላለሰ ከፊቷ ያለቅሳል፡፡ ሥዕሏም በል እንግዲህ ቸግሮህ ከሆነ እኔ ምንም የማደርግልህ ነገር የለኝም፡፡ እኔኑ ዉሰድና ሽጠህ ብላ አለችዉ፡፡ እሷም እንዳለችዉ ሥዕሏን ይዞ ወጣ፡፡ ከአጸደ ቤተክርስቲያኑ ሲደርስ እመቤታችን የልቡን መቁረጥ አይታ የምትሸጠኝ ከሆነማ እዚህ አስቀመምጠኝ እና ጩህ አለችዉ ፡፡ አስቀምጦት ድምጹን ከፍ አድረጎ ጮኸ፡፤

ሥዕሏ ሰዎቹ ሲመጡ እንዳይመቱህ  ተሸሸግ አለችዉ እና እንዲደበቅ አደረገችዉ፡፡ የገዳሙ መነኮሳት እና የአካባቢዉ ሰዎች ሰምተዉ ወዲያዉኑ ደረሱ፡፡ መጀመሪያ ሥዕሏን በተቀመጠችበት ቀጥሎ ሰዉየዉ በተደበቀበት አገኙት፡፡  የተሰበሰበዉ ሰዉ ሁሉ እንግደለዉ በማለት በቁጣ ተነሣሣ፡፡

debre-zemedo-mary[1]

የገዳሙ መምህር ግን በቅድሚያ የሠራዉን እንጠይቀዉ ብለዉ አቆዩት፡፡ ለምን ሥዕለ ሉቃስን ከተቀመጠችበት ቦታ አነሣሃት ሲሉም ጠየቁት፡፡ በየእለቱ ከፊቷ እየሄድኩ አለቀስኩ በመጨሻም እኔ ሽጠህ ብላ ስላለችኝ በመቸገሬ የተንሳ አምጥቻታለሁ አላቸዉ፡፡ የገዳሙ ሃላፊ መምህር በሉ የተቻላችሁን ያህል እርዱት ብለዉ የተሰበሰበዉን ሰዉ ሁሉ እንደየ አቅሙ አዋጥቶ በጊዜዉ ለእርሱ የሚበቃዉን ያህል ሰጥተዉ ከሸኙት በኋላ ሥዕለ ማርያምን ወደ ቦታዋ አስገብተዋታል፡፡

debre-zemedo-mary-with-kahnat[2]


References:-

ደ/ን ኅሩይ ባየ፤ ቅዱሳን መካናት፡፡ 36-37::

Images from:

[1] DIANA SPENCER. In search of St. Luke Ikons in Ethiopia, Journal of Ethiopian Studies, Vol. 10, No. 2 (JULY 1972), pp. 81.

[2]  Copyright © 2005 Michael Gervers, Ewa Balicka-Witakowska: Mazgaba Seilat 

 

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s