ሥዕለ ቅዱስ ደቅስዮስ


አዘጋጅ፡- ኃይለማርያም ሽመልስ facebook.com/ethioicons 

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በታህሳስ 22 ከሚዘከሩት ቅዱሳን መካከል ቅዱስ ደቅስዮስ ሲሆን ይህ ቅዱስ አባት የእመቤታችንን ተአምር ከፍቅሯ የተነሣ አሰባስቦ ያዘጋጀ አባት ነው፡፡ ይህ አባትም እረፍቱ በታህሳስ 22 የሚታሰብ ሲሆን፤ ሥዕሉም በቤተክርስቲያን ከሚሳሉ ቅዱሳን አንዱ ነው፡፡ በይበልጥም በተአምረ ማርያም የብራና መጽሐፍት ላይ ተሥሎ ይገኛል፡፡ ለዛሬ የዚህን ጻድቅ ሥዕል ከሥር ቀርቧል፡፡

ስለ ቅዱስ ደቅስዮስ ታሪክ ማወቅ ለሚፈልግ ከመረጃ መረብ[1] ያገኘሁት ጽሑፍ ከሥር ቀቧል፡፡ የቅዱስ ደቅስዮስ በረከት ከሁላችን ጋር ለዘለዓለሙ ጸንቶ ይኑር፡፡ አሜን፡፡

በዚህች ዕለት የብርሃን እናቱ እመቤታችን ለወዳጇ ለቅዱስ ደቅሲዮስ ሰማያዊ ወንበርና ልብስ ሰጥታዋለች፡፡በእመቤታችን ፍቅር ልቡ የነደደው ይህ ታላቅ አባት የእመቤታችንን ተዓምራቶቿን የጻፈላትም እርሱ ነው፡፡ እርሱም ከፍቅሩ ጽናት የተነሣ የእመቤታችንን የተአምራቷን መጽሐፍ ሰብስቦ አዘጋጀ፡፡

አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናቸ ክብርት እመቤታችንም ተገለጸችለትና መጽሐፉን በእጇ አንሥታ ይዛ ‹‹ወዳጄ ደውሲዮስ ሆይ! ይህን መጽሐፍ ስለጻፍክልኝ ባንተ ደስ አለኝ፣ አመሰገንኩህ፣ እንዳከበርከኝ እኔም አከብርሃለው›› አለችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከእርሱ ተሠወረች፡፡ ደቅሲዮስም እመቤታችንን ከመውዱ የተነሣ ፈጽሞ ደስ አለው፡፡ ፍቅሯም እንደ እሳት አቃጠለው፡፡ የእርሷን ክብር አብዝቶ ይጨምር ዘንድ ምን እንደሚያደርግ የሚሠራውን ያስብ ጀመር፡፡

ከዚህም በኋላ በዚያን ጊዜ ጾም ስለነበር ሰዎች አስቀድመው ሊያከብሩት ያልተቻላቸውን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ባበሠራት ቀን በዓሏን አከበረ፡፡ እርሱም የከበረ የሚሆን የልደትን በዓል ከማክበር አስቀድሞ በ8 ቀን አደረገ፡፡ ይኸውም ታኅሣሥ በባተ በ22ኛው ቀን ነው፡፡ ይኽችውም ሥርዓቱ እስካሁን ጸንታ ኖራለች፡፡ ሰዎቹም በዓሉን ባከበሩ ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው፡፡ በዚህም ጊዜ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናቸ ክብርት እመቤታችን በእጇ የከበረ ልብስ ይዛ ዳግመኛ ለቅዱስ ደቅሲዮስ ተገለጸቸለትና ‹‹አገልጋዬ የሆንክ ወዳጄ ደቅሲዮስ ሆይ! በዕውነት አመሰገንኩህ፣ በአንተ ደስ አለኝ፣ ሥራህንም ወደድኩ፡፡

በእኔም ደስ እንዳለህና የከበረ መልአክ ገብርኤል እኔን በአበሠረበት ቀን በዓሌን ስላከበርክ ሰውንም ሁሉ ስለእኔ ደስ ስላሰኘህ እኔም ዋጋህን ልሰጥህ መጥቻለሁ፤ አንተ በዚህ ዓለም እንዳከበርከኝ እኔም በሰው ሁሉ ፊት አከብርህ ዘንድ እወዳለሁ›› አለችው፡፡

ይህንንም ካለችው በኋላ ‹‹እርሷን ትለብስ ዘንድ ይህችን ልብስ እነሆ አመጣሁልህ፤ በላዩም ትቀመጥ ዘንድ ይህን ወንበር አመጣሁልህ ፡፡ ከሰው ወገን አንድ ስንኳ ይህችን ልብስ ሊለብሳት በዚህችም ወንበር ላይ ሊቀመጥ የሚቻለው የለም፡፡ ይህንን ነገሬን የሚተላለፍ ቢኖር እኔ እበቀለዋለሁ›› አለችውና ሰማያዊ ልብስና ሰማያዊ ወንበር ሰጠችው፡፡ እመቤታችንም ይህንን ተናግራ ከባረከችው በኋላ ከእርሱ ተሠወረች፡፡

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ደቅሲዮስ በዚሁ በዓለ ብሥራትን ባከበረበት ዕለት ታኅሣሥ 22 ቀን ካረፈ በኋላ ሌላ ኤጲስቆጶስ በተሾመ ጊዜ እመቤታችን ለቅዱስ ደቅሲዮስ የሰጠችውን ልብስ ለበሰ፣ በወንበሩም ላይ ተቀመጠ፡፡ ሰዎችም ይህን አይተው ‹‹እባክህ ይቅርብህ እመቤታችን እንዲህ ብላ ተናግራለችና›› ቢሉት በመታጀር ‹‹እርሱም (ደቅሲዮስም) ሰው እኔም ሰው፣ እርሱም ኤጲስቆጶስ እኔም ኤጲስቆጶስ›› ብሎ በትዕቢት ተናገረ፡፡ በወንበሩም ላይ እንደተቀመጠ ወድቆ ሞተ፡፡ ይህንንም ያዩ ሁሉ ከእመቤታችን ተአምር የተነሣ አደነቁ፡፡ እጅግም ፈርተው እመቤታችንን አከበሯት፡፡

ለቅዱስ ደቅስዮስ የተለመነች የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ ለእኛም ትለመነን፡፡

ምንጭ፡-

[1] https://www.facebook.com/jemal.aliyimer/posts/1409535919056937

http://ethiopia.deeds.utoronto.ca/ 

 

Leave a comment