ስለቅዱሳት መጻሕፍትና ቅዱሳት ሥዕላት ዐውደ ርእይ በደብረ ቀራንዮ አንቀፀ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት


ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሚገኘው የቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤ/ክ ደብረ ቀራንዮ አንቀፀ ተዋሕዶ ሰ/ት/ቤት በዓይነቱ ልዩ የሆነ ስለቅዱሳት መጻሕፍትና ቅዱሳት ሥዕላት ዐውደ ርእይ አዘጋጀተው በያዝነው የፍልሰታ ሱባኤ እያሳዩ ይገኛሉ፡፡

image

image

image

ስለ ቅዱሳት ሥዕላት ግንዛቤ ለማግኘትም ይህ ዐውደ ርእይ ጥሩ መድረክ ሲሆን ዐውደ ርእዩ የሚታየው በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ ነው፡፡ የሚታይበት ጊዜም ከቅዳሴ ውጪ ባሉ ሰዓታት ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 2፡00 ድረስ ነው፡፡ ዐውደ ርእዩ እስከ ነሐሴ 16 2008 ዓ.ም. ድረስ ይቆያል፡፡

image

ወደ ቦታው ለመሔድ የሚፈልጉ ደግሞ ጦርኃይሎች ከደረሱ በኋላ ቀራንዮ የሚለውን ታክሲ በመያዝ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መሔድ ይችላሉ፡፡ ባቡሩም ወደ ጦርኃይሎች ድረስ የሚያስኬድ በመሆኑ ለትራንስፖርት ምቹ ነው፡፡

ወደ ዐውደ ርእዩ ቢሔዱ የቅዱስ ሉቃስ ሥዕሎች የሆኑትን በደብረወርቅ የምትገኘውን ‹‹ወይኑት››፣ በተድባበ ማርያም የምትገኘውን ‹‹ሥዕለ አድኅኖ››፣ በጌቴሴማኒ የምትገኘውን ‹‹ሥርጉት›› እና በደብረ ዘመዶ የምትገኘውን ‹‹ግብጻዊት›› መመልከት ይችላሉ፡፡ ስለ እያንዳንዱ ሥዕል ታሪክ በቀጣይ የማቀርብ መሆኑን ከወዲሁ ለማሳወቅ እወዳለሁ፡፡

በተጨማሪም ስለ ‹‹ሥዕለ ቅድስት አርሴማ›› የተሰኘውን መጽሐፍ ዐውደ ርእዩ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

image

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s