ሐሙስ: የሰሙነ ሕማማት በቤተክርስቲያን ቅዱሳት ሥዕላት እይታ


በሰሞነ ሕማማት ከስቅለትና ከትንሣኤ በፊት ያለው ሐሙስ የተቀደሰ እና የተመረጠ ቀን ነው፡፡ ይህ እለት መቀደስ ብቻ ሳይሆን በእለቱ ከተፈጸሙት ታላላቅ ምስጢሮች የተነሣ በተለያየ መጠሪያ ይጠራል፡፡ ከእነዚህም መካከል ሕጽበተ እግር፣ ጸሎት ሐሙስ፣ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ እና የምስጢር ቀን ይጠቀሳሉ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሚሳሉት የጌታችን ሥዕሎች መካከል በዚህ የተቀደሰ እለት የተፈጸሙት ምስጢራት አንዱ ናቸው፡፡ በሥዕል ከሚገለጡት ጭብጦች መካከል ጌታችን የሐዋርያትን እግር ሲያጥብ፣ ጌታችን ከሐዋርያት ጋር ሆኖ ከቅዱስ ቁርባን ምስጢር ሲያካፍላቸው ሚያሳዩት ሥዕሎች ሰፊውን ቦታ ሲይዙ፡፡ ጌታችን በጌቴሴማኒ ሲጸልይ የሚያሳየው ሥዕል ግን በስፋት አይታይም፡፡

የሐሙስ እራት ሥዕል

ይህ ሥዕል በቤተክርስቲያን በስፋት የሚሣል ሲሆን አሣሣሉም ጌታጭን ከመሐል ሆኖ 6 ወይም 5 ሐዋርያት በቀኝ 5 ወይም 6 ሐዋርያት በግራ ሆነው ሁሉም ሙሉ ፊታቸውና ሁለት ዓይናቸው እየታየ ይሣላሉ፡፡ 5 ሐዋርያት ባሉበት ወገንም የአስቆሮቱ ይሁዳ ብቻ ግማሽ ገጽ ተደርጎ ሣላል፡፡ የሐዋርያት ሙሉ ገጽ መሆን ቅድስናቸውን ሲያመለክት የይሁዳ ግማሽ ገጽ መሆን ደግሞ እምነተ ጎዶሎ መሆኑን ያጠይቃል፡፡

 

ሆኖም ግን የቤተክርስቲያን ምስጢርን ከትምህርተ ሃይማኖት ጋር በማስተባበር የሚሣሉትንና የአሣሣል ትውፊት የጠበቁ ሥዕሎችን መጠቀም አሁን አሁን እየቀረ ነው፡፡ ነገር ግን ከዚህ በተቃራኒ ሐዋርያትን ሙሉ ገጽ ከማድረግ ልቅ ግማሽ ገጽ ተደርገው እየተሳሉ ይገኛል፡፡ አብዛኛው ምእመናንም ባለንበት ዘመን ከሉላዊነት ተጽእኖ የተነሣ የሚጠቀሙባቸው እና አንዳንድ ጊዜ በሠዓልያን ተሥለው ወደ ቤተክርስቲያን የገቡት ሥዕሎች ሥርዓተ ቤተክርስቲያን የሚያፋልሱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ይህ ዓይነት ሥርዓተ ቤተክርስቲያን የሚያፋልሱ ሥዕል ከሚታይበት ቤተክርስቲያን መካከል የቦሌ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተጠቃሽ ነው፡፡

thelastsupper12
ቦሌ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የሚገኘውና ሥርዓተ ቤተክርሰቲያን የሚያፋልሰው የጸሎተ ሐሙስ ሥዕል
የሊዮናርዶ ዳቪንቺ ሥዕል
የሊዮናርዶ ዳቪንቺ ሥዕል

በተለይ የሊዮናርዶ ዳቪንቺ ሥዕል ከፍተኛውን ተጽእኖ ያስከተለው ሥዕል ሲሆን፤ ይህንን ሥዕል መሠረት ተደርጎ የተጻፈና ‹‹ዘዳቪንቺ ኮድ›› የተሰኘ የክህደት መጽሐፍም ይገኛል፡፡ የዚህ ሥዕል በጣም መታወቅ ይህ የኑፋቄ መጽሐፍ በዓለም ላይ እንዲታወቅ አድርጎታል፤ ዳግመኛም የቤተክርስቲያን ሥዕሎች ለማያውቁ እና የውጭ ሥዕሎችን እንደትክክል ለሚወስዱ አንዳንድ ሰዎች  የዚህ ኑፋቄ ሰለባ ሊሆኑ ያስችላል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የብራና ላይ የተወሰኑ ሥዕሎች ላይ ሕብስቱንና ጽዋውን ብዙ በማድረግ እንዲሁም ገበታ ማእድ ብዙ በማድረግ ከቤተ ክርስቲያን የአሣሣል ትውፊት ውጪ  ብዙ ሥዕሎች ተሥለው ይገኛሉ፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታቸው ግን ኦርቶዶክሳውያን የቤተክርስቲያን ሥርዓት የጠበቁትን ሥዕሎች ብቻ መተቀም ይኖርባቸዋል፡፡

መልካም ሰሙነ ሕማማት ፡፡

Images from Mazgaba Seilat


Photographs copyright © 2005 Michael Gervers, Ewa Balicka-Witakowska, et al.

© ከኃይለማርያም ሽመልስ ሚያዚያ 2008 ዓ.ም

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s