ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሻጮችና ለዋጮችን እገረፈ ከቤተ መቅደስ ሲያወጣ

ሰኞ: የሰሙነ ሕማማት በቤተክርስቲያን ቅዱሳት ሥዕላት እይታ


ሰኞ

ስለ ቅዱሳት ሥዕላት የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ethioicons.wordpress.com እና facebook.com/ethioicons ይመልከቱ፡፡

ሰሙነ ሕማማት በመባል የሚጠራው ሳምንት የመጀመሪያው ቀን ሰኞ የሆሳእና በዓል ከተከበረ ማግስት የሚውል ሲሆን፤ ይህ እለትም መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፡፡ ይኸውም ጌታችን በሆሳዕና ዕለት ቢታንያ በምትባል መንደር አድሮ የነበር ሲሆን፤ በማግስቱም ከቢታንያ ሲወጣ ይራባል ቅጠል ያላትን በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ በዚህም ጊዜ ጌታችን ‹‹ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ፡፡›› ብሎ ረገማት፡፡ ማር 11፡11-14::

 

ከዚህም በተጨማሪ በዚህ እለት ጌታችን ወደ ቤተመቅደስ በሔደ ወቅት ምንም እንኳ ቤተ መቅደሱ የጸሎት ቤት ቢሆንም ሰዎች ቤተ መቅደሱን የንግድ ቤት በማድረጋቸው ጌታችን የእነዚህን ሰዎችና እና ሸቀጦች ከቤተ መቅደስ ያጸዳበትን ቀን ይዘከራል፡፡ ማር 15-18::

በተለይ ይህ እለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት ሥዕላትን በአገልግሎት ላይ እንዲውሉ በሐዲስ ኪዳን ያጸናበት እና ቁጥራቸው ከንዋየ ቅድሳት ጋር መሆኑን የገለጠበት ታላቅ የምስጢር ቀን ነው፡፡

መልካም ሰሙነ ሕማማት ፡፡

Images from Mazgaba Seilat


Photographs copyright © 2005 Michael Gervers, Ewa Balicka-Witakowska, et al.

© ከኃይለማርያም ሽመልስ ሚያዚያ 2008 ዓ.ም

Advertisements

2 thoughts on “ሰኞ: የሰሙነ ሕማማት በቤተክርስቲያን ቅዱሳት ሥዕላት እይታ

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s