ንብ በሚያረባ ሰው ላይ የተደረገ ተአምር


ብዙ ንብ ያለው ሰው ነበር፡፡ ከሰው ሁሉ ይልቅ ፈጽሞ ንቡ ይበዛለት ዘንድ ይወድ ነበር፡፡ ወደ አንዲት ሥርየኛ ሴት ሒዶ ንቤ ይበዛልኝ ዘንድ መዓርም ሰምም ከሰው ሁሉ ይልቅ ይበዛልኝ ዘንድ የምሠራውን ሥራ እንትመክሪኝ እለምንሻለሁ አላት፡፡ ያችም ሥራየኛ ሴት እኔስ ሥጋውን ደሙን በተቀበልህ ጊዜ ካፍህ አውጥተህ በዚያ ቀፎ ውስጥ ጨምረው ብዙ ንብ ሰምና ማርም ይሆንልሀል ብየ እመክርሀለሁ አለችው፡፡

በሁለተኛውም ቀን ወደ ቤተክርስቲያን ሒዶ ሥጋውን ደሙን ተቀብሎ እን ነገረች አደረገና ካፉ አውጥቶ በንቡ ውስጥ ጨምሮ አንዲት ሰዓት እልፍ አለ፡፡ ሁለተኛም ንብ ወዳለበት በተመለሰ ጊዜ ሥጋውን ካስቀመጠበት ከዚያ ቀፎ ውስጥ እጅግ ፍጹም ብርሃንና የእመቤታችን ሥዕል በዚያ ቀፎ ውስጥ በንቦች መካከል ተቀምጦ አየ፡፡ በደረቷም ከፀሐይና ከጨረቃ የሚያበራ ልጅን ታቅፋ ነበር፡፡

ይህን ምልክት ባየ ጊዜ ፅኑዕ ፍርሃት ፈራና ወደ ቄስ ሒዶ ያደረገውን ሁሉ በቀፎ ውስጥም ያየውን ነገረው፤ ቄሱ ግን ነገሩን አልተቀበለውም ነበር፡፡ ነገር ግን ያሳየህን ተመልከት እይ ብሎ አንድ ዲያቆን ከሱ ጋር ላከ፡፡ ዲያቆኑም ሒዶ ያ ሰው እንደተናገረው አይቶ በፍጹም ፍርሃት ተመልሶ ያየውን ለቄሱ ነገረው፡፡

ቄሱም ይህን ነገር ሰምቶ ሕዝቡ ሁሉ በፍጹም ተድላ ደስታ ይሰበሰቡ ዘንድ አዘዛቸውና ወደዚያ ቦታ ደረሱ፡፡ ያም ቄስ  ቀደዚያ ቀፎ ቀረበና ያን ፍጹም ብርሃን አይቶ ድንግል እመቤታችንም ሕፃኑን አቅፋ ከሕፃናት ጋራ በብዙ ንቦች መካከል አይቶ ፈጽሞ ፈራ፡፡ ቀፎውንም ተሸክመው ወስደው በታቦቱ ላይያኖሩት ዘንድ አዘዘ፤ ያችንም ሥዕል አውጥቶ በመንበሩ ላይ አስቀመጣት፡፡

እስከ ፍታቴው ድረስ ይቀደስ ዘንድ አዘዘ፤ ሥዕሊቱም ተመልሳ በታቦቱ ላይ ባለ በሥጋው አደረች፡፡ ቅዳሴውም እንደታዘዘ ተፈጸመ፡፡ ይችም ምልክት በአራቱ ማዕዘን ሁሉ ተረዳች፡፡ የሰሙም ሁሉ አደነቁ፡፡ እግዚአብሔርን አመሰገኑት አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች ክብርት እመቤታችንንም አመሰገኑዋት፡፡[1]


[1] 73ኛ ተአምር፡፡ በእንተ ብእሲ በዓለ ንህብ፡፡ 317-318፡፡

Advertisements

One thought on “ንብ በሚያረባ ሰው ላይ የተደረገ ተአምር

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s