ሥዕለ ሚካኤል፡ ቅዱስ ሚካኤል ሶምሶንን እንደረዳው


በቤተክርስቲያናችን በስፋት ከድርሳናቸውና ከገድላቸው አንጻር በስእል ያሸበረቁ ቅዱሳን መካከል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተጠቃሽ ነው፡፡ ሆኖም ግን በአብዛኛው ምእመናን ዘንድ ይህ የሊቀ መላእኩ ቅዱሳት ስእላት በስፋት ባለመሰራጨታቸው ምእመናን የሌሎች አብያተክርስቲያናት ሥርዓትና እምነት የሚያሰተላልፉ ሥዕሎችን ይጠቀማሉ[1]፡፡

በመሆኑም ይህንን ችግር ለመቅረፍና የበኩሌን ጠጠር ለመወርወር በማሰብ ከመላእኩ ቅዱስ ሚካኤል ድርሳነ ውስጥ በየካቲት 12 ቀን የሚታሰበውን የመስፍኑ ሶምሶንና የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕልን እነሆ፡፡ ሥዕሎቹ በብራና ላይ የተሣሉ ሲሆን በ18ኛው መ.ክ.ዘ. የተሠሩ ድረሳነ ሚካኤል መጽሐፍ ላይ ነው የሚገኙት፡፡ መልካም ንባብ፡፡

በየካቲት 12 ቀን መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልን እግዚአብሔር ወደ ረዓይታዊ ወደ ሶምሶን ላከው፡፡ ሶምሶንን የፍልስጤም ሰዎች ሊገድሉት በጠላትነት በተነሡበት ጊዜ ድል እስካደረጋቸውና እስከ ገደላቸው ድረስ መልአኩ ረዳት ሆነው፡፡ መልአኩ ኃይልን ሰጥቶት ሶምሶን ጠላቶቹን ሁሉ ድል አደረጋቸው፡፡ ከእርሱም በየቀኑ በአህያ መንጋጋ ሺህ ሺህ ሰው በመግደል ፈጽሞ አጠፋቸው፡፡ ከዚህም የተነሣ ሶምሶን ውኃ ጠምቶት ለሞት በደረሰ ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጾለት አጽናናው፤ ከአህያም መንጋጋ አጥንት ውኃን አፈለቀለትና ጠጥቶ ዳነ፡፡

ዳግመኛም የፍልስጤም ሰዎች በሶምሶን ድል በተነሡ ጊዜ ከሚስቱ ጋራ በመሻረክ ልዩ ዘዴ ፈጥረው ዐይኖቹን አሳውረው በማጥፋት ኃይሉ አድሮበት የነበረውንም የራሱን ፀጉር ላጭተው አሠሩት፡፡ ከዚህም በኋላ ለጣዖቶቻቸው በዓልን ባዘጋጁ ጊዜ ሶምሶንን ወደ ጣዖቶቻቸው ቤት ወሰዱት፡፡ በዚያም ሦስት ከሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ተሰብስበው ነበር፡፡

samson killing philistines and St. Micheal appearing to samson

ሆኖም የእግዚአብሔር መልእክተኛ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ለሶምሶን ተገልጾለት ኃይልን ሰጠው፡፡ ሶምሶንም የዚያን ቤት ምሰሶዎች ነቀላቸውና ቤቱ በላያቸው ላይ ወድቆ ከእርሱ ጋር ሁሉንም ገደላቸው፡፡ ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሐዋርያት የመላእክት አለቃ ንዑድ ክቡር የሚሆን የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ በዚህች ዕለት እናደርግ ዘንድ አዘዙን፡፡ የገናናው መልአክ የቅዱስ ሚካኤል ልመናው ጸሎቱ ለዘለዓለሙ ከእኛ ጋር ይኑር አሜን፡፡[2]

© በኃይለማርያም ሽመልስ 2008 ዓ.ም.

Photographs copyright © 2005 Michael Gervers, Ewa Balicka-Witakowska, et al.


[1] ኃይለማርያም ሽመልስ፡ ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት፡፡ ታሪክ፣ መንፈሳዊ ትርጉም፣ የሊቃውንት አስተምህሮ እና ሌሎችም . . .፡፡ 191፡፡

[2] Jemal Hassen Ali Yimer

 መዝገበ ሥዕላት፡ የቅዱሳት ሥዕላት መረጃ ቋት

Advertisements

One thought on “ሥዕለ ሚካኤል፡ ቅዱስ ሚካኤል ሶምሶንን እንደረዳው

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s