ንብ በሚያረባ ሰው ላይ የተደረገ ተአምር

ብዙ ንብ ያለው ሰው ነበር፡፡ ከሰው ሁሉ ይልቅ ፈጽሞ ንቡ ይበዛለት ዘንድ ይወድ ነበር፡፡ ወደ አንዲት ሥርየኛ ሴት ሒዶ ንቤ ይበዛልኝ ዘንድ መዓርም ሰምም ከሰው ሁሉ ይልቅ ይበዛልኝ ዘንድ የምሠራውን ሥራ እንትመክሪኝ እለምንሻለሁ አላት፡፡ ያችም ሥራየኛ ሴት እኔስ ሥጋውን ደሙን በተቀበልህ ጊዜ ካፍህ አውጥተህ በዚያ ቀፎ ውስጥ ጨምረው ብዙ ንብ ሰምና ማርም ይሆንልሀል ብየ እመክርሀለሁ አለችው፡፡ በሁለተኛውም ቀን ወደ ቤተክርስቲያን ሒዶ ሥጋውን ደሙን ተቀብሎ እን ነገረች አደረገና ካፉ አውጥቶ በንቡ ውስጥ ጨምሮ አንዲት ሰዓት እልፍ አለ፡፡ ሁለተኛም ንብ ወዳለበት በተመለሰ ጊዜ ሥጋውን ካስቀመጠበት ከዚያ ቀፎ ውስጥ እጅግ ፍጹም ብርሃንና የእመቤታችን ሥዕል በዚያ ቀፎ ውስጥ በንቦች መካከል ተቀምጦ አየ፡፡ በደረቷም ከፀሐይና … Continue reading ንብ በሚያረባ ሰው ላይ የተደረገ ተአምር

ሥዕለ ሚካኤል፡ ቅዱስ ሚካኤል ሶምሶንን እንደረዳው

በቤተክርስቲያናችን በስፋት ከድርሳናቸውና ከገድላቸው አንጻር በስእል ያሸበረቁ ቅዱሳን መካከል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተጠቃሽ ነው፡፡ ሆኖም ግን በአብዛኛው ምእመናን ዘንድ ይህ የሊቀ መላእኩ ቅዱሳት ስእላት በስፋት … Continue reading ሥዕለ ሚካኤል፡ ቅዱስ ሚካኤል ሶምሶንን እንደረዳው

መግቢያ ጠባቂዋ ሥዕለ ማርያም፡ PANAGIA PORTAITISSA

መግቢያ ጠባቂዋ ‹‹Panagia Portaitissa›› በመባል የምትታወቀውና ቅዱስ ሉቃስ ሣላቸው ከሚባሉ ቅዱሳት የእመቤታችን ሥዕላት መካከል ስትሆን በምስራቁ የባይዛነቲን ክርስቲያን ሀገር በየካቲት 4 በዓሏ የሚታሰብላት የእመቤታችን ሥዕል ናት፡፡ … Continue reading መግቢያ ጠባቂዋ ሥዕለ ማርያም፡ PANAGIA PORTAITISSA

የቅዱስ ኤፍሬም ሥዕል በቤተክርስቲያን

እንኳን ለቅዱስ ኤፍሬም የሥጋው ፍለሰት በዓል አደረሳችሁ፡፡ ይኽ ታላቅ ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬም ቅድስት ድንግል ማርያምን በእጅጉ ይወዳት የነበረ ሊቅ ሲኾን፤ ርሷንም ከመወድዱ የተነሣ ከሉቃስ ወንጌል ወበሳድስን ጸሎተ ማርያምን አውጥቶ በዕድሜዋ ልክ ፷፬ ጊዜያት ድረስ እየጸለየ የእመቤቴ ምስጋናዋ እንደ ሰማይ ከዋክብት … Continue reading የቅዱስ ኤፍሬም ሥዕል በቤተክርስቲያን