ሥዕለ በዓታ ለማርያም


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምለክ አሜን፡፡

ውድ ኦርቶዶክሳውያን የወላዲተ አምላክ የአሥራት ልጆች እንኳን ለእናታችን እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ፡፡

በጸሎት እና በሱባዔ እግዚአብሔርን ደጅ ጸንተውና ስእለት የበረከት ፍሬ የሆነችውን የቅድስት ድንግል ማርያም ወላጆች የሆኑት ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና በተባረከችና በተቀደሰች በታህሳስ 3 ቀን የዓለሙ ሁሉ ጌታ ክብርና መድኃኒት የሆነውን ጌታን ያስገኘችውን ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምን ለቤተእግዚአብሔር ያስገቡበት ዕለት ነው፡፡ ለዛሬም ስለ ሥዕለ በዓታ ለማርያም ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለአብነት ያህል እንመለከታለን፡፡

መግቢያ

ቅዱስ ኢያቄም እና ቅድስት ሐና ልጅ ያልነባራቸው መካኖች የነበሩ ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ ወደ እግዚአብሐርም ልጅ ብትሰጠን ለአንተ ቤት አገልጋይ እናረጋታለን በማለት ተሥለው ነበር፡፡ የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትን የሚሰጥ ቸርሩ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምን ነሐሴ 7 ጸንሰው ግንቦት 1 ወለዱ፡፡

የእመቤታችን እድሜ ሦስት ዓመት ሲሞላው ጠቢቡ ሰሎሞን “ሰነፎችደስ አያሰኙትምና ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልኽ ጊዜትፈጽመው ዘንድ አትዘግይ የተሳልኸውን ፈጽመው፤ ተስለኽ የማትፈጽም ብትኾን ባትሳል ይሻላል” መክ 5፡4-5 ብሎ የተናገረውን በማሰብ ባሏ ኢያቄምን ይኽቺ ብላቴና የብጽአት ገንዘብ እንደኾነች ታውቃለኽ ወስደን ለቤተ እግዚአብሔር እንስጣት አለችው፡፡ ርሱም ፍቅርሽ ይለቅልሽ ብዬ ነው እንጂ እኔማፈቃዴ ነው አለ፤ ኢያቄም ይኽነን ማለቱ ሐና እመቤታችንን በመካንነት ኑራ ያገኘቻት አንድያ ልጇ ናትና ከፍቅሯ ጽናትየተነሣ ተለይታት አታውቅም ነበርና ነው፡፡

ከዚኽም በኋላ ቅድስት ሐና ከቅዱ ኢያቄም ጋር በመሆን ወደ ካህኑ ዘካርያስ ወደሚገኝበት ቤተመቅደስ ልጃቸውን ወሰዷት፡፡ ኢያቄምና ሐና እግዚአብሔርን በማመስገን ካህኑ ዘካርያስን ‹‹ይኽቺ ብላቴና ተስለን አምላካችን በቸርነቱ የሰጠን ናትና ተቀበለን›› አሉት፡፡ ርሱም ቢያያት እንደ ፀሓይ የምታበራ እንደመብረቅ ግርማዋ የሚያስፈራ የምታበራ ዕንቈ ባሕርይ መስላታየችው፡፡

ወደ ቤተመቅደስ በወሰዷት ወቅትም ርሱም በአድናቆት ይኽቺን የመሰለች ፍጥረት ምን እናደርጋታለን፣ ምን እናበላታለን፣ ምንስ እናጠጣታለን፣ ምን እናነጥፍላታለን፣ ምን እንጋርድላታለን ብሎ ሕዝቡን ሰብስቦ ሲጨነቁ ለእስራኤል ደመና ጋርዶ መናን አውርዶ የመገበ፤ለኤልያስም በመልአኩ እጅ በመሶበ ወርቅ ኅብሥት የመገበ፤ለዕዝራ ሱቱኤልም በመልአኩ በቅዱስ ዑራኤል እጅ መልኩእሳት የሚመስል ጽዋዐ ልቡና ያጠጣው ልዑል እግዚአብሔርለእናትነት ወደ መረጣት ወደ እናቱ መልአኩ ፋኑኤልንላከላት (ዘፀ 16፡ 31፤ 1ኛነገ 19፡6፤ ዕዝ. ሱቱ. 13፥38-41)::

‹‹ወሶቤሃ ወረደ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት ወጸለላ በአክናፊሁ ወተለዐለ ላዕለ መጠነ ቆመ ብእሲ ወወሃባ ወመጠዋ ወዐርገውስተ ሰማይ›› ይላል በዚያን ጊዜ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወት ይዞረቦ ወረደ፤ ዘካርያስ ለርሱ የመጣ ሀብት መስሎት ሊቀበልቢነሣ ወደ ላይ ሰቀቀበት፤ ያን ጊዜ ጥበበ እግዚአብሔርአይመረመርምና ለዚኽች ብላቴና የመጣ ሀብት ይኾናል እስኪእልፍ አድርጋችኊ አኑሯት አለ፤ እልፍ አድርገው ቢያኖሯት ድንኩል ድንኩል እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ አንድክንፉን አንጽፎ አንዱን ክንፉን አጐናጽፎ ከመሬት የሰው ቁመት ያኽል ከፍ ብሎ ኅብስቱን መግቧት ጽዋውንአጠጥቷት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡

ሥዕለ በዓታ ለማርያም በኢትዮጵያ በቤተ ክርስቲያን

ከላይ በጥቂቱ የእመቤታችን ወደ ቤተመቅደስ የመግባቷ ታሪክ ሲሆን ከሥር ደግሞ እንዴት በቤተክርሰቲያናችን ይህ ታሪኳ እንደሚሣል እንመለከታለን፡፡ የወላዲተ አምላክ ቅዱስ ሥዕሎች ከጌታችን እና መድኃኒታችን ቅዱስ ሥዕሎች በመቀጠል በቤተክርስቲያናችን በብዛትም ሆነ በጭብጥ በስፋት የሚገኙ ሥዕሎች ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል የበዓታ ሥዕሎቿ አንዱ ሲሆን በተለያየ መልኩ ሊሣል ይችላል፡፡

በበዓታ ለማርያም ሥዕል ላይ የሚገባው የገጸ ባህርያት ብዛትም በሚሣልበት መደብ ስፋት እና ጥበት ሊለያይ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ሥዕሉ የሚሣለው በብራና ላይ ነከሆን ሚገቡት የካህናት ቁጥር ሊያንስ ይቻላል፡፡ በሌላ መለኩ ደግሞ በግድግዳ ላይ የሚሣል ከሆነ ደግሞ የሚገቡት ካህናት ቁጥራቸው ከፍ ሊል ይችላል፡፡ በአጠቃላይ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የበዓቷ ሥዕልን ለሁለት ከፍለን መመልከት እንችላለን፡፡ ይኸውም ቅዱስ ኢያቄም እና ቅድስት ሐና ወደ ቤተመቅደስ ሲያስገቧት እና ቤተመቅደስ በገባችበት ወቅት ቅዱስ ፋኑኤል ሕብስት አና ጽዋ ይዞ ሲወርድ ያለው ሥዕልን ነው፡፡

  1. ወደ ቤተመቅደስ ወላጆቿ ሲያስገቧት የሚያሳየው ሥዕል

ይህ ሥዕል ደግሞ በቤተ ክርስቲያናችን ረጅም እድሜ ካስቆጠሩት ቅዱስ ወንጌሎች መካከል በ15ኛው መ.ክ.ዘ. የተሠራውና በክብራን ገብርኤል ቤተክርስቲያን የሚገኘው ወንጌል ላይ ወደ ቤተመቅደስ ስትገባ የሚያሳየው ሥዕል ይታያል፡፡ በዚህ ሥዕል ላይ ደግሞ ቅዱስ ኢያቄምና እና ሐና ሲያስገቧት እና ለቅዱስ ዘካርያስ ሊሰጡ ሲዘጋጁ የሚያሳይ ሥዕል ነው፡፡

MG-1982.056.036

በ18ኛው መ.ክ.ዘ. በሰቆጣ አካባቢ በሚገኘው የውቅሮ መስቀል ቤተክርስቲያን ደግሞ በምዕራብ በኩል የነገረ ማርያም ታሪኮች የሚታዩ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ወደ ቤተመቅደስ ስተገባ እና ካህኑ ዘካርያስ ሲቀበላት ያሳያል፡፡ ከዚህ ሥዕል አጠገብም በቤተመቅድስ ተቀምጣ መጽሐፍ ስታነብ ይታያል፡፡

MG-1993.015.011

ከዚህም ሌላ በደብረ ዮሐንስ ኪዳነ ምሕረትም በ19ኛው መ.ክ.ዘ. የተሣለ ሥዕል ላይ በደቡብ ወገን እመቤታችን ወደ ቤተመቅደስ ስትገባ ይታያል፡፡  በዚህኛው ሥዕል ላይ ካህኑ ዘካርያስ አጎንብሶ ሲቀበላት ይታያል፡፡

MG-1993.016.037

በደብረ ፀሐይ ቤተክርስቲያን በ20ኛው መ.ክ.ዘ. የተሠራ የበዓታ ለማርያም ሥዕል ላይ ደግሞ ካህኑ ዘካርያስ ተቀምጦ ሳለ ወላጆቿ ወደ ቤተመቅደስ ይዘዋት ሲሄዱ ካህናተ ኦሪት ደግሞ በማሕሌት ሲያወድሱ ይታያል፡፡

MG-1993.013.013

በጨለቆት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ደግሞ በቤተክርስቲያኑ በደቡብ ክፍል የበዓታ ለማርያም ሥዕል ይታያል፡፡ ይህ ሥዕል ላይ ደግሞ ቅድስት ሐና እመቤታችንን ለካህኑ ዘካርያስ ከምድር ከፍ አድርጋ በመያዝ እመቤታችንን ልተሰጥ ስትል ይታያል፡፡ ካህናተ ቤተ መቅደስ ካህኑ ዘካርያስን በኋላ ሆነው ሲያወድሱ ይታያል፡፡ ይህ ደግሞ በደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ በ19ኛው መ.ክ.ዘ. የተሠራውን የዚህ ጭብጥ ሥዕል ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ነገር ግን የደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተከርስቲያን ሥዕል በጨለቆት ከሚገኘቅ አቻው የሚለየው ካህኑ ዘካርያስ ጸንሐ ይዞ እና እመቤታችን እየተራደመች መታየቱ ይለያል፡፡ ከሥር ከብዙ በጥቂቱ ሌሎች የበዓታ ለማርያም ሥዕሎችን ይመልከቱ፡፡

  1. የመልአኩ የቅዱስ ፋኑኤል ሕብስቱን

እስከ አሁን ከተመለከትኩዋቸው በዓታ ለማርያም ሥዕሎች ላይ በደብረ ፀሐይ ቤተክርስቲያን በ20ኛው መ.ክ.ዘ. ከላይ የተጠቀሰው ቤተክርስቲያን ላይ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል ከምድር ከፍ አድርጎ ሲመግባት የሚያሳየው የሚያስደነቅ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪም የመልአኩ ከሰማይ ሲወርድ ነገር ግን ሕብስት እና ጽዋው ለላህኑ ዘካርያስ አለመሆኑን ሲያሳይ ሆኖም ግን ለእመቤታችን ለእርሱ ከልክሎ ለእርሷ ሲመግባት የሚተርከውን ታሪክ አገላለጹ ግሩም የሚያስብል ነው፡፡

© ከኃይለማርያም ሽመልስ ታህሳስ 2008 ዓ.ም.


ምንጭ፡

በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፡፡ መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ታኅሳስ ፫ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም. http://www.mekrezetewahdo.org/2013/12/blog-post_7855.html  በ12/12/2015.

Photographs copyright © 2005 Michael Gervers, Ewa Balicka-Witakowska, et al.  

Advertisements

One thought on “ሥዕለ በዓታ ለማርያም

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s