ሥዕለ ቅዱስ ዳዊት፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን


በነገው ዕለት የሚከበረውን የሕዳር ጽዮን በዓልን ምክንያት በማድረግ የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ ሊያንጽ አስቦ ያልተፈቀደለትን ነገር ግን እውነተኛ ማደሪያ ታቦት ስለሆነችው ጽዮን እና ስለ ነገረ ልደቱ ስለተገለጸለት ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርቲያን ምን እንደሚመስል ከሥር እንመልከት፡፡

ቅዱስ ዳዊት በእግዚአብሔር ዘንድ እንደልቤ ተብሎ የተነገረለት፣ በትሕትናው፣ በንስሐው የተመሰከረለት እንዲሁም በብዙ ሀብታት የሚታወቅ ነቢይ እና ንጉሥ ነበር፡፡ ይህ ቅዱስ ለረጅም ዘመናት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተከርስቲያን ሥዕላቸው ያለመቋረጥ ተሥሎ  ከሚገኙት ቅዱሳን መካከል ነው፡፡ ሥዕሉም በብራና፣ በግድግዳ እንዲሁም በገበታ ሥዕሎች ላይ ተሥሎ ይገኛል፡፡

ለምሳሌ በጥንታዊነታቸው ከሚታወቁት አብያተክርስቲያናት መካከል በገነተ ማርያም ቤተከርስቲያን በ13 መ.ክ.ዘ. የግድግዳ ሥዕል፣ በአባ ገብረመስቀል እና ጊዮርጊስ ቤተከርስቲያን ግድግዳ ላይ (14/15ኛው መ.ክ.ዘ.)፣ በጉንዳጉንዶ የሚገኝ የብራና ሥዕል (15ኛው መ.ክ.ዘ.)፣ 17ኛው መ.ክ.ዘ. ተአምረ ማርያም ብራና ላይ፣ 18ኛው መ.ክ.ዘ. መዝሙረ ዳዊት እና በIES (IES-3792) ከሚገኙት ገበታ ሥዕል በገና እየደረደረ የሚታዩት ሥዕሎች ለዚህ ማሳያ ናቸው፡፡

ቅዱስ ዳዊት በቤተክርስቲያናችንም በስፋት በገና ሲደረድር ይሣላል፡፡ በዚህ የአሣሣል ጭብጥም ቅዱስ ዳዊት ለረጅም ዘመናት በቤተክርስቲያናችን የእርሱን ቅዱስ ሥዕል ለአገልግሎት ከቅዱስ መዝሙር በተጨማሪ ለአገልግሎት ስትጠቀምበት ኖራለች፡፡

በገና ሲደረድር እንዳለው በብዛት የሚገኙ ባይሆንም ሌሎች ቅዱስ ዳዊትን ጭብጦች ተሥለው ለአገልግሎት ውለዋል፡፡

  1.  ዳዊት ጎሊያድን በእግዚአብሔር ሲያሸንፈው
  2. በዓለ እረፍታ ለማርያም ሥዕል ላይ እያረጋጋት በበገናው የሚታየው ሥዕል ለምሳሌ በተአምረማርያም እና በሴቶች ወገን ባሉ ግድግዳዎች ላይ ይታያል፡፡
  3. ዳዊት በጎችን እየጠበቀ እና ነቢዩ ሳሙኤል ቅዱስ ዳዊትን ሲቀባው፣ በቅዱስ ሚካኤል ድርሳን ላይ ደግሞ ቅዱስ ዳዊትን እንዲቀባው ቅዱስ ሚካኤል
  4. የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ ልታንጽ አይገባም ተብሎ በነቢዩ ሲነገረው
  5. በቤተ እግዚእብሔር ሲጸልይ
  6. በመዝሙረ ዳዊት ላይ ደግሞ መዝ 50 ላይ ያለውን ጥቅስ ተይዞ ተጸጽቶ እየሰገደ ሲጸልይ
  7. በዮርዳኖስ ባሕር አጠገብ እየሰገደ ሲጸልይ
  8. በአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገድል ላይ ነፍሳቸውን በበገና መዝሙር እያረጋጋ ተሥሏል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት እንደምሳሌ ከብዙ በጥቂቱ ቅዱስ ዳዊት በሥዕል የተገለጠባቸው ጭብጦች ናቸው፡፡

ከቅዱስ ዳዊት እና ከወላዲተ አምላክ በረከት ረድኤት ፈጣሪያችን ይክፈለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር


Photographs copyright © 2005 Michael Gervers, Ewa Balicka-Witakowska, et al.

© ከኃይለማርያም ሽመልስ ኅዳር 2008 ዓ.ም.

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s