ሥዕለ ኪዳነ ምሕረት


ኦርቶዶክሳውያን እንደ እግዚአብሔር ቸርነትና እና ቅዱሳን አማላጅነት መጠን በዚህ ጦማር በየቀኑ በዚህ የቅዱሳን ነቢያት ጾም ወቅት ልዩ ልዩ የሆኑ የቅዱሳን ሥዕላትን ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡ እንዲቀርብ የምትፈልጉት የቅዱስ ሥዕል ካለ በዚህ አድራሻ አሊያም በፌስቡክ ገጽ መጠየቅ ይቻላል፡፡

በዛሬው ዕለት ኪዳነምሕረት የምትከበርብት ወርሐዊ በዓል እንደመሆኑ መጠን  በእመቤታችን የምሐረት ቃልኪዳን ከተቀበለችበት ሥዕል እንጀምራለን፡፡ Click for pdf.


ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ኪዳን ነው፡፡  እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል፡፡[1] ‹‹የኪዳነ ምሕረት›› በመባል የሚታወቀው ሥዕል በቤተክርሰቲያናችን በስፋት ከሚሳሉት የወላዲተ አምላክ ሥዕል ጭብጦች ውስጥ አንዱ ሲሆን በሁለት መልኩ ሊሣል ይችላል ይኸውም፡-

ሀ. ከጌታችን ኢየሱስ ቃልኪዳን ስትቀበል በጎሎጎታ የሚያሳየው ሥዕል አንደኛው ሥዕል ነው፡፡ይህ ሥዕል እንደ ቤተክርስቲያኑ ስፋት የሚጨመረው ጭብጥ ሊለያይ ይችላል፡፡ ለምሳሌ በዚህ ሥዕል ዘይቤ ላይ የሚታዩት መላእክት ቁጥራቸው ሊበዛ አሊያም ሊያንስ ይችላል፡፡ ይህ ሥዕል ላይ እመቤታችን እና ጌታችን ቆመው አሊያም ተቀምጠው ጌታችን በቅዱሳን እጆቹ የእናቱን ቅዱሳን እጆች በመያዝ ቃል ኪዳን ሲገባላት አሊያም በቅዱሳት እጁ ቃል ሲገባላት የሚያሳይ ዓይነት ሥዕል ነው፡፡

በዚህ መልኩ እመቤታችን ከተሳለችባቸው አብያተክርስቲያናት መካከል ጎርጎራ ደብረ ሲና(17ኛው መ.ክ.ዘ.)፣ አብርሐወ አጽብሐ (19ኛው መ.ክ.ዘ.)፣ አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ መቐለ(20ኛው መ.ክ.ዘ.)፤ ከጥንታውያን ብራና መጻሕፍት ከተመለከትን በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ግምጃ ቤት የሚገኘው የ17ኛው መ.ክ.ዘ. ተአምረ ማርያም ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ለ. በሁለተኛው የአሣሣል ዘይቤ ደግሞ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ሲያከብሯት ማለትም የክብር አክሊል ሲያቀዳጀዋት የሚያሰየው ሥዕል፡፡ ይህ ሥዕል በሁለት መልኩ በሥዕል ተገልጦ በስፋት ይተያል፡፡ የመጀመሪያው አብና ወልድ ተመሣሣይ ገጽ እና ነጭ የፀጉር ዓይነት ተደርጎላቸው ሲሣል፤ በሁለተኛው ሥዕል ላይ ግን ወልድ እግዚአብሔር ፀጉሩ ጥቁር ተደርጎ ይሠራል፡፡ የእግዚአብሔር አብ ሥዕል ላይ ግን ለውጥ አይደረግም፡፡ መንፈስ ቅዱስም በሁለቱም ዓይነት ውክልናዎች ላይ በርግብ አምሳል ሆኖ ይሣላል፡፡

በዚህ ጭብጥ ከተሣሉ  እበያተ ክርቲያናት መካከል መሐል ዘጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን (18ኛው መ.ክ.ዘ.)፣ ጨለቆት ሥላሴ (18 ኛው መ.ክ.ዘ.) ይጠቀሳሉ፡፡ ይህ ጭብጥ በስፋት በአሁኑ ዘመን ተሰራጭቶ እና የኪዳነ ምሕረት የሚባለው ሥዕል ነው፡፡

በመጨረሻም በግብፅ ሀገር ባሉ ክርስቲያን ወገኖቻችን ‹‹የመገለጧ ማርያም›› በመባል የምትታወቀው የቅድስት ድንግል ማርያም በተለምዶ የኪዳነ ምሕረት ሥዕል በስፋት ይታወቃል፡፡ በምእመናኑ ዘንድም በስፋት በአገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል ነገር ግን ቅዱሳት ሥዕላት በሚወክሉበት ጭብጥ ለአገልግሎት ቢውሉ ከሥርዓተ ቤተክርስቲያንና ከአስተማሪነት አንጻር የተሻለ ይሆናል፡፡

http://zeitun-eg.org/warraq.htm

የወላዲተ አምላክ አማላጅነት በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ ለዘላለሙ ፀንቶ ይኑር፡፡ አሜን፡፡

ወስብሐት እግዚአብሔር፡፡

ወለወላዲቱ ድንግል፡፡

ለመስቀሉ ክብሩ፡፡


[1] http://silemariam.blogspot.com/2010/12/blog-post_12.html

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s