‹‹ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት›› የመጽሐፍ ምረቃ


‹‹ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት›› የተሰኛው መጽሐፍ በማኅበረ ቅዱሳን ሕንፃ 3ኛ ፎቅ በ20/2/2008 ዓ.ም. በዕለተ ቅዳሜ ይመረቃል፡፡ እርሶም በእለቱ በመገኘት ስለቅዱሳት ሥዕላት ያለዎትን ግንዛቤ በመጨመር በረከትን ይሸምቱ፡፡

መጽሐፉን የአዘጋጀው ኃይለማርያም ሽመልስ ሲሆን በማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሥነ ሥዕል ዘርፍ አገልጋይ ሲሆን መጽሐፉም ሙሉ በሙሉ ገቢው ለማእከሉ አገልግሎት ማስፈጸሚያ እንዲውል በስጦታ የተበረከተ ነው፡፡

ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: ታሪክ፣ መንፈሳዊ ትርጉም፣ የሊቃውንት አስተምህሮ እና ሌሎችም. . .
ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት: ታሪክ፣ መንፈሳዊ ትርጉም፣ የሊቃውንት አስተምህሮ እና ሌሎችም. . .

ትንሽ ስለ መጽሐፉ

 • በቅዱሳት ሥዕላት ዙርያ አሣሣል ዘይቤውን በተመለከተ በዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሥዕልን ከሌላው ዓለም ሥዕላት መለየት ያስችላል፡፡
 • ብርቅዬ የሆኑ ቅዱሳት ሥዕላት መካከል 1500 ዓመት ያስቆጠረ ሥዕልና በጻድቁ አቡነ መብአ ጽዮን የተሣለ ሥዕል በውስጡ ማካተቱ
 • የቀደምት የቤተክርስቲያን አበው ሊቃውንት በቅዱሳት ሥዕላት ዙርያ ያስተማሩትን ትምህርት ያስቃኛል፡ ለምሳሌ፣
  • ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
  • ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
  • ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ
  • ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንደርያ
  • ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እና ሌሎችም
 • ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የተገኙ የቁፋሮችንና ፍለጋ ውጤቶችን ባካተተ መልኩ ለመናፍቃን መልስ የሚሰጥ መሆኑ ወዘተ. . . ከመጽሐፉ ውስጥ ከሚገኙ ነጥቦች መካከል ናቸው፡፡

ስለቤተክርስቲያን ቅዱሳት ሥዕላት ታሪክ፣ መለያ ገጽታዎች፣ ትምህርተ ሃይማኖታዊ ምስጢሮችን ከአባቶች አስተምህሮ፣ የቤተክርስቲያን ቅዱሳት ሥዕለትን በተመለከተ ያጋጠማቸውን ወቅታዊ ፈተናዎች ከነመፍትሔዎቻቸውን ያየዘውን መጽሐፍ በዕለቱ በመገኘት ያስመርቁ፡፡

በእለቱ በመገኘት የምርቃቱ ተካፋይ እንዲሆኑ የማእከሉ ሥነሥዕል ዘርፍ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

Advertisements

One thought on “‹‹ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት›› የመጽሐፍ ምረቃ

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s