የቅድስት በርብራ ሥዕል በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ውድ የክርስቶስ ቤተሰቦች በባለፉት ጊዜያት ወጥቶ ከነበረው ጽሑፍ መካከል ባለ ሦስት ተከታታይ ዕትሞች ስለ ቅድስት አርሴማ ሥዕል (ክፍል 1ክፍል 2 እና ክፍል 3) እና በዘመናችን በቤተክርስቲያን የሚታየውን ፈተና ከተለያዩ የመረጃ ምንጮችን በማስደገፍ አቅርቤ ነበር፡፡

ነገር ግን በጽሑፉ ላይ ለመገልጽ እንደተሞከረው በብዙ ምእመናን ለአገልግሎት የዋለው የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በመባል የሚታወቁት ሥዕላት የሌሎች ቅዱሳን መሆናቸውን አንዳንድ ምእመናን በተረዱ ወቅት ለመቀበል ቸግሯቸዋል፡፡ ሲቀጥልም በቅድስት አርሴማ ስም የተሸፈኑትን ቅዱሳን አንስትን እንደቅዱሳን ከመቁጠርና ከማክበር ብሎም የቅዱሳኑን ታሪክ ገድል ለማወቅ ከመጣር ይልቅ የመደንገጥና የመጠራጠር ብሎም ክርስቲያናዊ ያለሆኑ ምላሾችን ሲሰጡ ተመልክቻለሁ፡፡

ሆኖም ግን ይህ ሁሉ የመረጃ ማነስና የቤተክርስቲያን መሪ አካላት በደንብ ለምእመናን ትክክለኛውን ሥዕል እንዲለዩ ባለማድረጋቸው፣ አሳታሚና አከፋፋዮች ደግሞ የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ሳይወጡ አባቶችን ሳያማክሩ ያገኙትን ሥዕል የቅድስት አርሴማ ሥዕል በማለት ማሰራጨታቸው እና መረጃው ያለቸው መምህራነ ወንጌል መንጋውን ባለመምራታቸው የተከሰተ ጉዳይ እንጂ ለመረጃው ስህተትነት ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም፡፡ ነገር ግን ከላይ የተዘረዘሩት ነገሮች ባለመፈጸማቸው በግልጽ በምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት በየድረገጻቸው የሰማዕታቱን ሥዕላት እንደየስማቸው ለምእመናኖቻቸው የሚያሰራጩት ሥዕላትን እንደቅድስት አርሴማ ሥዕል የቤተክርስቲያን ልጆች እንዲጠቀሙ ሆኗል፡፡

በመሆኑም የዛሬውን ጽሑፍ እንዳዘጋጅ ያደረገኝ በአብዛኛው ምእመን ዘንድ በስፋት ‹‹የቅድስት አርሴማ ሥዕል›› በሚለው የምትታወቀውን የቅድስት በርብራን (ታሪኳን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተሣለውን የቅድስት በርብራን ሥዕል ለማሳየት ነው፡፡

የቅድስት በርብራ ሥዕል በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን

ቅድስት በርብራ በቤተክርስያናችን በስንክሳር ላይ ከሚታወቁ በሥዕል ከተገለጹ ቅዱሳን መካከል ናት፡፡ በሥዕል ደግሞ በቤተክርስቲያን የግድግዳ ላይና በብራና የተአምረ ማርያም ላይ ታሪኳ ከሥዕሏ ጋር በመተባበር ተሥሎ ይገኛል፡፡ በግድግዳ ላይ ተሥሎ ሥዕሏን የምናገኘው በጥንታዊ የ13ኛው መ.ክ.ዘ. ሥዕል በገነተ ማርያም ሲሆን፤ በብራና ላይ ደግሞ በ18ኛው መ.ክ.ዘ. ተአምረ ማርያም ላይ የ11ኛው ተአምር ላይ ከተወደደችው እሕቷ ዑልያና ጋር አብራ ተሥላለች፡፡ ስለሁለቱ ሥዕሎች ተጨማሪ ማብራሪያ ከሥዕሎቹ ጋር ከሥር ቀርቧል፡፡

  1. የገነተ ማርያም የቤተመቅደስ የቅድስት በርብራ እና የቅድስት ዑልያና ሥዕል

ላሊበላ አቅራቢያ በሚገኘው የገነተ ማርያም ቤተክርስቲያን የሰሜን መተላለፊያ ሁለተኛው ዓምድ በስተደቡብ በኩል የቅድስት በርብራ እና የቅድስት ዑልያና ሥዕል ይገኛል፡፡ ይህ ሥዕል የተሣለው በዓምዱ ግድግዳ ላይ የአል-ሴኮ (al secco on plaster) ዘዴን በመጠቀም ሲሆን ቀለማቱ ደግሞ የተፈጥሮ ቀለማትን ናቸው፡፡ በቅዱሳኑ ሥዕል መካከል የሚከተለው ጽሑፍ ተጽፎ ይገኛል፡-

‹‹ቅድስት በርብራ ምስለ እሕታ ዑሊያና ሰላ ወጸልያ በእንቲአነ››

To see the large version of the image click here and here.

  1. በተአምረ ማርያም ላይ የሚገኘው የቅድስት በርብራ እና የቅድስት ዑልያና ሥዕል

ቅድስት በርብራ እና ቅድስት ዑልያና በተለያዩ ሁለት የተአምረ ማርያም መጻሕፍ ላይ ተመሳሳይ ተአምራትን በሚገልጹ ክፍልች ላይ ሥዕላቸው ተሥሎ ይገኛል፡፡ ተአምሩ በአጭሩ ሲተረክ ቅድስት በርብራ እና ዑልያና ወደ ቤተክርስቲያን በሚሔዱበት ወቅት ሌቦች አግኝተዋቸው የሚበሉትን ዳቦ በጉልብት ይወስዱባቸዋል፡፡ በዚህም ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሌቦቹን ዳቦ ወደ ድንጋይ ትቀይርባቸዋለች፡፡ ይህንንም ተመልክተው ሌቦቹ ንስሐ ገብተው ይመነኩሳሉ፡፡

ይህንን ድንቅ ተአምርን የሚገልጹ ሁለት ሥዕሎችን ያገኘው ሲሆን አንደኛው ተአምረ ማርያም በጉንዳጉንዶ ማርያም ገዳም ዕቃ ቤት የሚገኝ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ብራና ላይ የተጻፈ ሲሆን ሥዕሎቹም በ18ኛው መ.ክ.ዘ. የሁለተኛው የጎንደር የአሣሣል ዘይቤ ይንጸባረቅባቸዋል፡፡ ሥዕሉም በገጽ 31 (Folio Reference: 31r) ላይ ይገኛል፡፡ የዚህኛው ከሁለተኛው ብራና የሚለየው እመቤታችን አትታይም ነገር ግን ሌቦቹ ሲቀሟቸው የሚያሰየው ድርጊት ብቻ ይታያል፡፡

11th miracle
ቅድስት በርብራ እና ዑልያና ወደ ቤተክርስቲያን በሚሔዱበት ወቅት ሌቦች አግኝተዋቸው የሚበሉትን ዳቦ በጉልብት ሲወስዱባቸው

To see the large version of the image click here.

ሁለተኛው መጽሐፍ እንደመጀመሪያው መጽሐፍ በ18ኛው መ.ክ.ዘ. በሁለተኛው የጎንድር የአሣሣል ዘይቤን በመከተል የተሣለ እና በጉንዳጉንዶ ማርያም ገዳም የሚገኝ ነው፡፡ ይህኛው መጽሐፍ ላይ ግን ሌቦቹ ዳቦን ሲወስዱ ከሚያሳየው ድርጊት በተጨማሪ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሌቦቹን ዳቦ ወደ ድንጋይ ስትቀይረው ይታያል፡፡

11th miracle; Barbara and Juliana robbed  of their food in the way to the church.VM turns food to stones in the mouth of the thieves another
ቅድስት በርብራ እና ዑልያና ወደ ቤተክርስቲያን በሚሔዱበት ወቅት ሌቦች አግኝተዋቸው የሚበሉትን ዳቦ በጉልብት ሲወስዱባቸው እና መቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሌቦቹን ዳቦ ወደ ድንጋይ ስትቀይረው

To see the large version of the image click here.

በመጨረሻም አባቶቻችን የሰሩትን ድንቅ ስራ እና የቅደሳኑን ገድ በማንበብ በረከታቸውን መለመን መማጸን እንጂ ይህ ሥዕል የቅድስት አርሴማ ካልሆነ ትክክል አይደለም አልቀበልም ማለት ተገቢ አይደለም፡፡ ዳግመኛም ከቅድስት አርሴማ ብቻ ሳይሆን ከቅድስት በርብራ፣ ከቅድስት ዑልያና እና ሌሎች ቅዱሳት አንስት በረከት ለመቀበል መትጋት ይገባናል፡፡

 የሰማዕታቱ በረከት ይድረሰን ይቅርታ ልመናቸውና በረከታቸው ከእኛ ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን፡፡


Photographs copyright © 2005 Michael Gervers, Ewa Balicka-Witakowska, et al.

© ከኃይለማርያም ሽመልስ መስከረም 2007 ዓ.ም

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s