የቅዱስ ሩፋኤል ሥነ ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

እንኳን ለሊቀ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ በዓል (ጳጉሜን 3) አደረሳችሁ:: ለዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሩፋኤል አሣሣል ምን እንደሚመስል እና በቤተመቅደስ የቅዱስ ሥዕሉን አቀማመጥ ነው፡፡

መግቢያ

ጳጉሜን 3 የመላአክት አለቃ የከበረ መልአክ የቅዱስ ሩፋኤል መታሰቢያ ነው ። ይኸውም ትጉሃን ቅዱሳን ሰማያውያን ከሚሆኑ ከመላአክት አለቆች ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል ቀጥሎ 3ተኛ ነው።

ጳጉሜን 3 ለምን የቅዱስ ሩፋኤል በዓል ይከበራል?

በጳጉሜን 3  ዕለት ተዝካሩ መደረጉ ስለ 2 ነገር ነው የመጀመሪያው በዓለ ሢመቱ ስለሆነ ነው።

ዳግመኛም የእስክንድርያው ሊቀጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ መሬት ውስጥ 3 ድስት ሙሉ ወርቅ አግኝቶ በአንዱ በድስት ሙሉ ወርቅ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት አሰርቷል። ከእንዱም አንዲቱ ከእስክንድርያ ውጭ በአለች ደሴት ላይ በቅዱስ ሩፋኤል ስም ቤተክርስቲያን አሰርቶ ስራዋን ጨርሶ እንደዛሬይቱ በአለች ቀን ቀደሳት።

  • ቅዱስ ሩፋኤልና ዓሣ አንበሪው

ምእመናን ከቤተክርስቲያን ውስጥ እየፀለዩ ሳሉ እንሆ ቤተክርስቲያኒቱ ተንቀጠቀጠች ተናወጠች ታወከች ። በመረመሩም ጊዜ ከባህር አንባሪዎች በአንዱ ታላቅ ዓሣ አንባሪ ላይ ተሰርታ አገኙዋት። ዓሣ አንባሪውም ከቦታው ሳይንቀሳቀስ ኑሮ ነበር። በላዩ የሰው ሁሉ እግር በበዛና በከበደው ጊዜ ቤተክርስቲያኒቱን ያፈርሳት ዘንድ ሰይጣን አወከው።

ምእመናንና ጳጳሱ ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱ ቅዱስ ሩፋኤል ተልኮ ፡ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ጸንትህ ቁም ከቦታህም አትንቀሳቀስ ብሎ ዓሣውን በጦር ወጋው። ያን ጊዜም ዓሣ አንባሪው በቦታው ጸንቶ ቆመ አልተንቀሳቀሰም። በዚችም ቤተክርስትያን ብዙ ውስጥ ብዙ ድንቅ ተአምራት ተደረገ።

የዋህ የምህረትና የረድኤት መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከስራዎቹ አንፃር በተለያየ ስም ይጠራል ለአብነት ያክል

  • “ፈታሄ ማህጸን” ይባላል። እናቶች ሲወልዱ ምጥ እንዳይበዛባቸዉ የሚራዳ መልአክ ስለሆነ አያሌ ክርስቲያኖች ማርገዛቸዉን ካወቁ ጀምሮ ድርሳኑን በማንበብ መልኩን በመድገም ጠበሉን በመጠጣት ሰዉነታቸዉን በመቀባት ይለምኑታል፡፡እንደ እምነታቸዉ ጽናት ይደረገላቸዋል፡፡
  • “ዐቃቤ ኖኀቱ ለአምላክ” ይባላል፡፡ ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠበቅ በመሆኑ ።
  • “መራሔ ፍኖት” ይባላል፡፡ ጦቢትን በቀና መንገድ መርቶታልና፡፡
  • “መላከ ክብካብ” ይባላል፡፡ ጦቢያና ሣራን ያጋባ ጋብቻቸዉን የባረከ በመሆኑ፡፡

የቅዱስ ሩፋኤል ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ቅዱስ ሩፋኤል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዓበይት ከሚጠቀሱና በሥዕል ከተገለጡ የሠራቸው ተአምራት መካከል ለጦቢት ዓይኑን ሲያበራለት፣ ወለተ ራጉኤልን ተቆራኝቷት የነበረውን ጋኔን እንዳስወጣ እና ዓሣ አንበሪውን በመስቀል ባለበት እንዲጸና ሲያደርግ ይሣላል፡፡ በስፋት ባይሆንም አንዳንድ ጊዜ ቅዱስ ሩፋኤል በምስለ ፍቁር ወልዳ ሥዕል ላይ ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል ጋር ተደምሮ ይሣላል፡፡

የቅዱስ ሩፋኤል ሥዕል በቤተመቅድስ አቀማመጥ

ቅዱስ ሩፋኤል በቤተመቅድስ የመቅደሱን በስተደቡብ ምዕራብ የሚገኘውን መግቢያ ላይ ከቅዱስ ሚካኤል ፈርኦንና ሠራዊቱን ሲያሰምጥ ከሚታየው ሥዕል አጠገብ ይሣላል፡፡ በዚህ መግቢያ ላይም የሚሣለው ዓሣ አንበሪውን በመስቀሉ ኃይል ሲያቆመውና ካህናተ እግዚአብሔር በቤተክርስቲያኑ ውስጥ እያሉ ይሣላል፡፡ ይህም የቤተክርስቲያን ጠባቂነቱን ያመለክታል፡፡ የቤተመቅደሱ በር ትልቅ ከሆነ ደግሞ ከላይ ከተገለጸው ጭብጥ በተጨማሪ የጦቢትን ዓይን ሲያበራለት የሚያሳየው ታሪክ ሊጨምር ይችላል፡፡

በዚህ ዕትም ደግሞ በተለያዩ ዘመናት በቤተክርስቲያን ሠዓሊያን ቅዱስ ሩፋኤልን የሣሉትን ሥዕል ከሥር ለአብነት ቀርቧል፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል ቆርቆር ማርያም ትግራይ፡ በ13/14 መ.ክ.ዘ. Rufael 13 or 14 wall painting Qorqor Maryam large

ቅዱስ ሩፋኤል ቆርቆር ማርያም ትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኝ ሥዕል፡፡ ሥዕሉ ላይ ቅዱስ ሩፋኤል የካህናት ልብስ ለብሶ እና አኪልል ተጎናጽፎ ይታያል፡፡ ሥዕሉ በ13/14 መ.ክ.ዘ. እንደተሣለ ይገመታል፡፡

Rufael dangelat Church of Virgin Mary 17th C.

Rufael dangelat Church of Virgin Mary 17th C.

በዳንግላት በሚገኘው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ የመቅደሱ በስተደቡብ ምዕራብ በኩል የሚገኝ የቅዱስ ሩፋኤል ሥዕል፡፡ ሥዕሉ የተሣለው የተፈጥሮ ቀላማትን አዋሕደው በመጠቀም በጨርቅ ላይ  በ17ኛው መ.ክ.ዘ. ነበር፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል የምስለ ፍቁር ወልዳ ሥዕል ላይ ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል ጋር፡፡ Rafael with Micheal and Gabriel in the Icon Virgin Mary 20 C. large

ቅዱስ ሩፋኤል የምስለ ፍቁር ወልዳ ሥዕል ላይ ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል ጋር፡፡ ሥዕሉ የገበታ ሥዕል ሲሆን የተሠራው በ20 ኛው መ.ክ.ዘ. ነው፡፡

ሊቀ መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ዓሣ አንበሪውን በመስቀል ባለበት እንዲጸና ሲያደርግ 20 መ.ክ.ዘ.

ቅዱስ ሩፋኤል ዓሣ አንበሪውን በመስቀል ባለበት እንዲጸና ሲያደርግ፡፡ ሥዕሉ የተሠራው በ20 ኛው መ.ክ.ዘ. በመቐለ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ነው፡፡

*** ማሳሰቢያ ከላይ የተገለጡት የቅዱስ ሩፋኤል ሥዕሎች እና የአቀማመጥ ሒደት ብቻ እንዳልሆነ አንባቢው እንዲገነዘብ እጠይቃለሁ፡፡***

የከበረ የመላእክት አለቃ የሩፋኤል ይቅርታ ልመናውና በረከቱ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን፡፡


© ከኃይለማርያም ሽመልስ ጳጉሜ 2007 ዓ.ም.

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s