ቅ/ሥዕላት፡ እግዚአብሔርንና ቅዱሳንን መውደዳችንን መግለጫዎች


  • አንባቢው እስቲ እንድ ጥያዌ ልጠይቅህ/ሽ?
  • እግዚአብሔርን እና እርሱ ያከበራቸውን ቅዱሳንን ትወዳቸዋለህ?
  • መልስህ አዎን ከሆነ፤ እንዴት ብዬ እጠይቃለሁ?
  • ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርንና ቅዱሳኑን እንዲሁም  መውደዷን ቅዱሳት ሥዕላት በመጠቀም ትገልጻለች፡፡ እንዴት አድርጋ ፍቅሯን ቅዱሳት ሥዕላት በመጠቀም ቤተክርስቲያን ትገልጻለች ካልክ መልሱን ከሥር አንብብ/ቢ፡፡ click for pdf.

ቅዱሳት ሥዕላት በቤተክርስቲያን ሰፊ አገልግሎት እና ዓላማ ያላቸው ሲሆን በዋናነት ደግሞ ለማስተማሪያ፣ ለሥርዓተ አምልኮ ማስፈጸሚያነትና ምእመናን ፍቅራቸውን ለመግለጽ፣ ለማስታወስ እና ለሥዕሉ ባለቤት መታሰቢያ ለማድረግ ነው። ይህ ደግሞ ከሥዕሉ ባለቤቶች ርዳታን እገዛን ምልጃንና በረከትን ለመቀበል ነው። “የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው” ምሳ 10፡ 7  እንዲል።

እንዴት ቅዱሳት ሥዕላት የፍቅር መግለጫ ሊሆኑ ይቻላሉ?

ፍቅር ወይም መውደድ ከሚገለጽባቸው አንዱ መንገድ የወደደው ስለተፈቀረው ወይም ስለተወደደው ሰው (አካል) ዘወትር ያስባል፣ ባለው ጊዜ፣ ሀብትና ጉልበት የፍቅሩን መግለጫ በተለያየ መንገድ ይገልጻል፡፡ ከመገለጫዎቹ መካከል የተለያዩ ስጦታዎችን በመስጠት (ለምሳሌ ሰዎች ለሚወዷቸው ሰዎች እንደ ፍቅራቸው ዓይነት የተለያዩ በቀለም ሆነ በዓይነት አበባዎች ያበረክቱላቸዋል፡፡)፣ ከወደዱት ሰው (አካል) ጋር ግንኙነት ያላቸውን ቀናትን በማስብ (ለምሳሌ የተወለዱበትን፣ የተጋበቡበትን፣ ልጅ ያገኙበትን ወዘተ . . )፣ ያንን ሰው (አካል) የሚያስታውን ነገሮች በክብር እንዲሁም በአቅርቢያቸው በማድረግ ፍቅራቸውን መውዳዳቸውን ብሎም ለሚወዱት ሰው ያላቸውን ቦታ ይገልጻሉ፡፡

ቅዱሳት ሥዕላት ደግሞ ከላይ ተጠቀሱትን የፍቅር መገለጫዎች ምእመናን እንዲያደርጉ በማገዝ ይረዳሉ፡፡ ከፍ ወዳለም የመንፈስና የነፍስ ልእልና ያደርሳሉ፡፡ ይህንን ለመረዳት ከሥር ያለውን እንድ ምሳሌ እንመልከት፡፡ (ከዚህ ሥር ቀጥሎ ያለው ምሳሌ በቅርቡ ለንባብ ከቀረበው ‹‹ ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት›› መጽሐፍ ገጽ 64-66 የተወሰደ ነው፡፡)

በሕይወተ ሥጋ ያለማንኛውም ሰው ይኑሩም በሥጋ ይረፉም የዘመዶቹን ፎቶግራፍ በቤቱ ፤ በመኝታ ቤቱ ወይም በቢሮው በክብር ይሰቅላቸዋል ፤ ወደ ተሰቀለውም ፎቶ ግራፍ በየጊዜው ያተኩራል። በሚመለከትበትም ወቅት ደስታ እና ፍቅር ይሰማዋል። ፎቶውን እየተመለከተ በሚያስብበት ጊዜም ከፎቶው ባለቤት ጋር ያሳለፋቸውን ጊዜ ያስባል።  ይኽውም አንደኛ ፍቅሩን ለመግለጽ ሁለተኛ ለማሰብ እና ለማስታወስ  ነው።[1]

ፍቅሩም ሲጸናበትም  ፎቶ ግራፉን አንስቶ ይስመዋል። አንድ ሰው  ይህንን ሲያደርግ ቢታይም  እንደተለመደ እና ተቀባይነት ያለው ድርጊት ተደርጎ ይቆጠራል ነገር ግን ለክርስቶስ እና ቅዱሳኑ ሲሆን ግን በመናፍቃን ዘንድ እንደ ክፉ ምግባር ይቆጠራል። ጌታችን በወንጌሉ ግን “ከእኔ ይልቅ አባቱንና እናቱን የሚወድ ለእኔ አይገባም ፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁንና እና ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ አይገባውም” በማለት አስተምሮናል።

በዚህ ምሳሌ ስንቀጥልም አንድ ሰው ከባለቤቱ እና ከልጆቹ በተለያየ ምክንያት በሚርቅበት ወቅት ከእርሱ ጋር ያለውን የቤተሰቡን ፎቶ በሚመለከትበት ወቅት ምንም ዓይነት ፍቅር እና ናፍቆት ካልተሰማው ይህ ሰው ባለቤቱንና ልጆቹን በእውነት ይወዳቸዋልን? የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል።

ልክ እንደ ሰውየው አንድ ክርስቲያንም የጌታችንን እና የቅዱሳኑን ሥዕል በሚመለከትበት ወቅት

  • ምንም ዓይነት የፍቅር እና ናፍቆት ስሜት ካልተሰማው አንዲሁም
  • በሥዕሉ ፊት በጸሎትና በመዝሙር ለማመስገን እና ለመስግድ ፍላጎት ከሌለው

ይህ ክርስቲያን በእውኑ ጌታችንን ይወደዋልን፣ ከእርሱስ ጋር አብሮ መኖርን ይሻልን፣ ሰውየውስ ክርስቲያን ነውን? የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል።  ሐዋርያው ጳውሎስ ግን ልሄድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለው በማለት ነበር ያስተማረው።[2]

ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖችም በሚያከናውኗቸው የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ውስጥ ቅዱሳት ሥዕላት ሲሣለሙ በሕይወት ያለ የቅርብ ክርስቲያን ወገናቸውን እንደመሳለም ይቆጥሩታል። ሊቁ አባ ጽጌ ድንግልም በድርሳኑ ከመ ይትፌሣህ ሕፃን ሶበ ይሬኢ እሞ፤እትፌሣህ አንሰ ሥዕለኪ በርእይ ወበተሳልሞ ድንግል ሆይ ሕጻን ልጅ እናቱን ባየ ጊዜ እንደሚደሰት እኔም ሥዕልሽን በማየትና በመሳለም እደሰታለሁ።[3] እንዲሁም

አባ ጽጌ ድንግል የድንግልን መከራነና ስደት በማሰብ ሲያመሰግን
አባ ጽጌ ድንግል የድንግልን መከራና ስደት በማሰብ ሲያመሰግን

«ሥዕልኪ ጽግይት ላህያ ከመዝኑ፡ ትኤድም፡፡ በዓለም፡፡ እፎ ይሤኒ በሰማይ ላህየ ገጽኪ ማርያም. . .፤ ማርያም ሆይ መልኳ አበባ የመሰለ (ደስ የምታሰኝ) ሥዕልሽ በዚህ ዓለም እንዲህ የምታምር ከሆነ በሰማይማ የፊትሽ መልክ ምን (እንዴት) ያምር (ክብርሽ እንዴት ይበልጥ?) የአንቺን ደስታ እጠግብ ዘንድ በሕልም ተገለጪልኝ ዝናብ ሊያጠፋው የማይችለው እሳት ፍቅርሽ አንድዶኛልና።» [4] በማለት ያለውን ጥልቅ ፍቅር እና ደስታ ሥዕሏን በማየትና በመሳለም እንደሚያገኝ ተናገረ።

በዚህ መሠረት በሥርዓተ ሃይማኖትም ምእመናን የጌታችን የክርሰቶስን፣ የድንግል ማርያምን፣ የመላእክትን፣ የጻድቃንን የሰማዕታትን ቅዱሳት ሥዕላትን በቤተ ክርስቲያን፣ በቤታቸው፣ በጸሎት ቤታቸው እንዲሁም በጸሎት መጻሕፍቶቻቸው የሚያደርጉት እና የሚስሙት ፍቅራቸውን ለመግለጽ፣ ለማሰብና ለማስታወስ እንዲሁም ከሥዕሉ ባለቤቶች ርዳታን እገዛን ምልጃንና በረከትን ለመቀበል ነው።

እኛም የወዳጆቻችን የቅዱሳንን ሥዕላትን እያየን ፍቅራችንን ብንገልጽ ከእነርሱም በረከት ረድኤት ብንለምን ምንድን ነው ኃጢአቱ? የቅዱሳን ርዳታ ደግሞ በገቢረ ተአምራትም ጭምር ነው፡፡ በተአምራቱም ለፈውስ፣ ክፉ አጋንንትን ለማራቅ ወዘተ… ምእመናን ይጠቀሙባቸዋል።

‹‹ ኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት ሥዕላት›› መጽሐፍ ገጽ 64-66፡፡   © ከኃይለማርያም ሽመልስ ነሐሴ 2007 ዓ.ም.

ዋቢ መረጃዎች


[1] ክብረ ቅዱሳት ሥዕላት። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሃይማኖትና ሥርዓት ። The Ethiopian Orthodox church Faith and Order. http://www.ethiopianortodox.org. David Withun. A defense of the Holy Icons. ማኅበረ ቅዱሳን ነገረ ቅዱሳን – Á (ነገቅªê)።34።

[2] David Withun.A defense of the Holy Icons.

[3] ሊቀ ጠበብት አስራደ ባያብል፣ማኅሌተ ጽጌ። ክፍል ሦስት።35።

[4] ዝኒ ከማሁ።40።

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s