የወንጌል ላይ ቅዱሳት ሥዕላት በቤተክርስቲያን


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ባህልና ታሪክ ያላት ድንቅ ሀገር ስትሆን ከዚህ ባህል ውስጥ ደግሞ የሥነ ሥዕል ጥበብ ባህልና ታሪኳ አንዱ ነው። ኢትዮጵያውያን የተቀደሱ ሥዕላትን መጠቀም የጀመሩት በንግሥተ ሳባ ልጅ ቀዳማዊ ምኒልክ አማካኝነት ሕገ ኦሪትን፣ ሌዋውያን ካህናትንና ታቦተ ሕጉን ከእሥራኤል ሀገር ሲረከቡ አብረው በታቦተ ሕጉ ላይ ተሥለው የነበሩትን ሥዕለ ኪሩብን በተረከቡ ወቅት ነበር፡፡

ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ክርስቲያናዊ ጭብጥ ያላቸውን ቅዱሳት ሥዕላት መጠቀም የተጀመረው በአብዛኛው ምሁራን ዘንድ በ4ኛው መ.ክ.ዘ መሆኑ በስፋት ይጠቀሳል። በዚህ ዘመንም ቅዱሳት መጻሕፍትም ከጽርዕ ወደ ግዕዝ መተርጎም ጀምሩ። ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር አብሮም ወጥ በሆነ መልኩ የመጻሕፍት አጻጻፍ እንዲሁም የአውሳብዮስ የቀኖና ሰንጠረዥና የያዛቸው ጌጣጌጦች ትናንሽ የወንጌላውያን ቅዱሳት ሥዕላት መሣል አብሮ ወደ ሀገራችን መጣ።1

እነዚህ የወንጌላውያን ሥዕላት በስፋት የሚታዩት በወንጌሉ የመጀመሪያው ክፍል ነበር፡፡ ሥዕሎቹም የሚሣሉት ወንጌላዊው ቆሞና መጽሐፍ ይዞ አሊያም ተቀምጦ በመጽሐፍ ላይ እየጻፈ ተደርጎ ነው፡፡ በአቡነ ገሪማ ገዳም የሚገኙት ሁለት ጥንታዊያን የብራና ወንጌሎች ለምሳሌ መውሰድ ይቻላል።

ገሪማ ፩ እና ፪ [Garima 1 and 2] በመባል የሚታወቁት እነዚህ መጻሕፍት በ5-7ኛው መ.ክ.ዘ. የተጻፉ ሲሆን በዓለማችን ላይ ካሉት እና በዚህ ዘመን በሥዕልና በተለያዩ ሐረጋት ተውበው ከተጻፉት በጣት ከሚቆጠሩ ብርቅዬ መጻሕፍት በዕድሜው ቀዳሚ ናቸው።2

በእነዚህ መጻሕፍት ውስጥም የአውሳብዮስን የቀኖና ሠንጠረዥ፣ የሕንጻ ላይ ጥበብ ጭብጦች፣ የእንስሳትና የአሞራ ሥዕሎችን የያዙ ወንጌል ናቸው። የገሪማ ፪ ብራና መጽሐፍ የወንጌላውያኑ ሥዕላት ይገኙበታል። ከአባ ገሪማ ወንጌል በተጨማሪ በሀገራችን ረዥም ዕድሜ ካስቆጠሩት የወንጌል መጽሐፍት አንዱ በሆነው በሐይቅ እስጢፋኖስ በሚገኘው ወንጌል ላይም የወንጌላውያኑ በወንጌሉ የመግቢያ ክፍል ላይ ይታያል ሥዕሎች ይገኛሉ፡፡

Four Gospels St. Mark. Parchment, c. 1320. Dabra Hyq Estifanos.
Icon of St. Mark. Parchment, c. 1320. Dabra Hyq Estifanos.

ሌላኛው ወንጌል ደግሞ የክብራን ገብርኤል ወንጌል (14/15 መ.ክ.ዘ.)3 ለቤተክርስቲያን በወንጌል ላይ የቅዱሳት ሥዕላት አጠቃቀም ማሳያ ነው፡፡ እነኚህ ለአብነት ተጠቀሱ እንጂ ይህንን እውነታ የሚመሰክሩ ብዙ የወንጌል መጻሕፍት ይገኛሉ፡፡

ይህ ጽሑፍ አንባቢው በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ለመጽሐፍ ቅዱስ እና ለቅዱሳት ሥዕላት የሰጠችውን ትልቅ ስፍራ እንዲረዳ ያለመ ነው፡፡ ዳግመኛም አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት ቤተክርስቲያን ቅዱሳት ሥዕላትን ለአገልግሎት መጠቀም በድንገት የተከሰተ ሳይሆን ታሪካዊ፣ ትውፊታዊና ሃይማኖታዊ ዳራ ያለው መሆኑን ግንዛቤ እንዲኖረው የታሰበ ነው፡፡

በመሆኑም የአባቶቻችንን ድንበር ሳናፈርስ እነርሱ ሰርተውልን ባስረከቡን ሥርዓት ጸንተን የክብሩ ወራሽ የስሙ ቀዳሽ እንዲያደርገን የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአበሔር


 

1 የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ እስከ ፳፻ ዓ.ም።14።

Claire Bosc- Tiesse. Spirits and materials of Ethiopian Icons.

Marilyn E. Heldmann. African Zion the sacred art of Ethiopia 119.

2 ራድዮ ካርበን 14 (Radiocarbon dating 14) በመጠቀም በተደረጉ ጥናቶች መሠረት ከ5ኛው መ.ክ.ዘ. መጨረሻ እስከ 6ኛው መ.ክ.ዘ. መካከል እንደተጻፉማረጋገጥ ተችሏል። ይህ ደግሞ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን የቅርጽ ጥበቃ፣ ቱሪዝምና ቤተመጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ። ዜና ቤተክርስቲያን ሚያዚያ 2005።

Amharic and English version April 2013. Dessie Keleb. Some Notes on the oldest llustrated Ethiopic manuscript ‘The Gospels of Abba Garima’. Journal of Ethiopian church studies. No. 1 (August 2010).p 88.

The Metropolitan Museum of Art፡ Page from an Illuminated Gospel, late 14th century

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s