ቅድስት አርሴማ፡ ትክክለኛው የቤትርስቲያን ሥዕሏ የቱ ነው? ክፍል ሁለት


በባለፈው ሳምንት በወጣው ‹‹ቅድስት አርሴማ፡ ትክክለኛው የቤትርስቲያን ሥዕሏ የቱ ነው?›› በተሰኘው ጽሑፍ ላይ በይደር ያለፈና በቀጣዩ ጽሑፍ የሚዳሰስ ርዕስ ነበር፡፡ ይኸውም ቅድስት አርሴማ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት እንዴት እንደሣሏትና ቅድስት አርሴማ ተብለው የተጠቀሱት ቅዱሳት አንስት አጠር ያለ መግለጫ ከአሣሣል መለያዎቻቸው ጋር ነበር፡፡ click for pdf

በቀጠሮ መሠረት ቀጣዩና ሁለተኛው የቅድስት አርሴማ ሥዕልን በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት እንዴት እንደሚሣል የሚያትተው ጽሑፍ እነሆ፡፡

በመጀመርያ በባለፈው ጽሑፍ ያለተዳሰስ ነገር ግን መዳሰስ የነበረበት ርዕሶችን አንስቼ ልለፍ

ቅዱሳት አንስት እነማን ናቸው፣ በቤተክርስቲያንስ እንዴት ይሣላሉ?

ቅዱሳት አንስት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መርጦ ካስከተላቸው አንድ መቶ ሃያ ቤተሰቦች መካከል ሰላሳ ስድስቱ ሴቶች ሲሆኑ፤ የእነርሱን አሠረ ፍኖት ተከትለው ስለስብከት፣ ስለእግዚአብሔር እና ስለሃይማኖታቸው ሲሉ ንጽሕናን ቅድስናን ገንዘብ አድርገው የኖሩትን ሴቶችን እንዲሁም እስከ ደም ጠብታ ለጌታችን የመሰከሩ ሴት ሰማዕታት ቅዱሳት አንስት በመባል ይታወቃሉ፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ብእሲተ አብርሃም ሣራን በሃይማኖትና በምግባር የሚመስሏትን ሴቶች ሁሉ ‹‹ቅዱሳት አንስት›› ብሎ ጠርቷቸዋል፤ 1ኛ ጴጥ 3፡5፡፡

ቅዱሳት አንስትም በቤተክርስቲያናችን ሲሣሉ ገድላቸውን መሰረት በማድረግ ከሠሯቸው ዐበይት ድርጊቶችን ተመርጠው ይሣላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቅዱሳት አንስት በቤተክርቲያን ሲሣሉ

  • ፀጉራቸውን ተሸፋፍነው እና
  • ምንም ዓይነት ጌጣጌጦችን ሳያደርጉ ይሣላሉ፤ 1ኛ ቆሮ 11፡6፡፡

ቅድስት አርሴማም ሆነ ከሥር የምንመለከታቸው ቅዱሳት ሰማእታት ወገናቸው ከቅዱሳት አንስት ሲሆን በቤተክርስቲያን እንዴት እንደሚሣሉ ከአጭር መግለጫ ጋር ቀርቧል፡፡

ቅድስት አርሴማ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት እንዴት ትሣላለች?

ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ቅድስት አርሴማ ከቅዱሳት አንስት ወገን በመሆኗ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ይሁን በሌሎች ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት (ኦርየንታል ሆነ ምስራቅ ኦርቶዶክስ) ስትሣል ፀጉሯን ተሸፋፍና ትሣላለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ገድሏን መሠረት በማድረግ በብዙ ዓይነት ድረሰት ትሣላለች፡፡ ነገር ግን በስፋት ከሚታዩት ሥዕሎቿ ላይ የተወሰኑ ክርስቲያናዊ ምልክቶች (Iconographic Symbols) ይታያሉ፡፡ እነዚህም፡-

  • ስለ ክርስቶስ ብላ ለተቀበለችው መከራ መስቀል ይዛ
  •  የሰማዕትነት ጽዋን መቀበሏን ለማመለክት ጽዋ ይዛ
  •  ሰይጣንና ዓለምን ድል አድርጋ መንገሥተ ሰማያት መግባቷን ለማመልከት ዘንባባ ይዛ ትሣላለች፡፡

ነገር ግን (ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች) ሁሉም በአንድ ላይ ሁልጊዜ ላይታዩ ይችላል፡፡ ይህ ማለት ግን እነዚህን ምልክቶች የሌለው ወይም የጎደለው ሥዕል ቅድስት አርሴማን አይወክልም ስህተት ነው ማለት አይደልም፡፡ እንደ የቤተክርስቲያኑ የአሣሣል እና መሳያ መደብ (ግድግዳ፣ ብራና፣ ገበታ ወዘተ. . .)የሚጨምሩት አሊያም ወይም የሚያጎድሉት ጭብጥ ሊኖር ይችላል፡፡ ከሥር የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ቅድስት አርሴማን ወክለው የሚጠቀሙባቸውን ሥዕሎችን እንመልከት፡፡

  • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ቅድስት አርሴማ ከቅዱሳት አንስት ወገን በመሆኗ ሁልጊዜ ስትሣል ፀጉሯን ተሸፋፍና ትሣላለች፡፡ የቅድስት አርሴማ ረዥም እድሜ ያስቆጠረ በቤተክርስቲያናችን የተሣለ ሥዕል የት እና ምን መደብ ላይ እንደተሠራ ጥናትና ምርምር የሚያስፈልገው ነገር ነው፡፡

ሆኖም ግን ካሉኝ መረጃዎች በመነሣት ቢያንስ በ15ኛው መ.ክ.ዘ. ገደማ (በኮሕሎ ዮሐንስ ቤ/ክ ሚገኘው ገድለ ሰማዕታት) የተሣሉ ሥዕሎች ማግኘት ይቻላል፡፡

በ20ኛው መ.ክ.ዘ. ማብቂያና አሁን ባለንበት የ21ኛው መ.ክ.ዘ. መጀመሪያ ላይ ደግሞ የሰማዕቷ ታሪክ እየታወቀ ሲመጣ በዚያኑ ልክ በእርሷ ስም የሚጠሩ የተሣሣቱ ሥዕሎችን ጨምሮ ሥዕሎቿ በቤተክርስቲያን ሠዓሊያን በስፋት ባይሆንም መሣል ጀምሯል፡፡

ከሥር ደግሞ የቤተክርስቲያን ትውፊት ታሪክና የአሣሣል ዘይቤን ተከትሎ የተሣሉ የቅድስት አርሴማን ሥዕል እንመለከታለን፡፡

ቅድስት አርሴማ ሥዕል st Arsema Circa 17 Century Ethiopian panel painting Icon
ቅድስት አርሴማ ሥዕልCirca 17 Century
በመጀመሪያው የጎንደር አሣሣል ዘይቤ የተሣለ የገበታ ላይ የቅድስት አርሴማ ሥዕል፤ ከላይ የተጠቀሱት 3ቱ ምልክቶች አይታዩም፡፡
20150528_100236_1_bestshot
ሥዕል ሀ. በሠዓሊ ቀሲስ አማረ ክብረት የተሣለና በአ.አ. ቦሌ ሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን በሴቶች መግቢያ በር ላይ የሚገኘው የቅድስት አርሴማ ሥዕል፡፡
2015-04-06 09.00.42
ሥዕል ለ. በሠዓሊ ዘሪሁን ገ/ወልድ በቀሲስ አማረ ክብረት የተሣለውን የቅድስት አርሴማን ሥዕል መሠረት በማድረግ የተሣለ ሥዕል፡፡ (ለሁለቱም ሥዕሎች 21ኛው መ.ክ.ዘ.)

SONY DSC

በሠዓሊ ታደሰ የማነ የተሣለ በገነተ  ማርያም ቤ/ክ የሚገኝ ቅድስት አርሴማ ሌላኛው የሰማዕቷ ሥዕል ነው፡፡ 21ኛው መ.ክ.ዘ.

ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ቤተክርስቲያን በጣም ሰፊ በመሆኗ በውስጧ የሚገኙት ሁሉንም አድባራት ገዳማትና ቤተመዘክሮችን አካሎ በጥናትና ምርምር የተደገፈ መረጃ እስካሁን አዘጋጁ የሌለው ቢሆንም፤ ለመግቢያ ያክል ግን የኢትዮጵያ ሠዓሊያን እንዴት በተለያዩ ዘመናት እንደሣሏት ይህ ጽሑፍ ፍንጭ ይሰጣል፡፡

ከዚህም ሌላ በቤተክርስቲያን የሚገኙት የቅድስት አርሴማ ሥዕሎች ወጥ በሆነ መልኩ ካልተሰናዳ (ለሌሎች ቅዱሳንም ያስኬዳል) በስተቀር ሌሎች የጻድቋ ሥዕሎች የሉም ማለት አያሰኝም፡፡ በመጨረሻም የቤተክርስቲያን ጥበብ በምልአት ስላልተጠና አሁን የቀረበው መረጃ በቂ አለመሆኑን አንባቢው እንዲገነዘብ አዘጋጁ መልእክቱን ያስተላልፋል፡፡

  • የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዘንባባ አስይዛ እንዲሁም በቤተደናግል አብረዋት የነበሩት ቅዱሳት አንስት ሠርተው ይሸጡት ከነበሩት ሥራዎች ጋር ተሥላ ይገኛል፤ ከላይ የተጠቀሱት 2ቱ ምልክቶች አይታዩም፡፡

httpwww.copticplace.comSaints_ELives_of_SaintsRhipseme.html

(http://www.copticplace.com/Saints_E/Lives_of_Saints/Rhipseme.html

  • የአርመን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

የአርመን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅድስት አርሴማን ከሣለችበት መንገድ አንዱ ንጉሥ ድረጣድስን በእግዚአብሔር ኃይል ጥላ ረግጣ የሚያሳይ

ሥዕል ሀ.20120801041202!St._Hripseme

https://en.wikipedia.org/wiki/File:St._Hripseme.jpg  ጽዋውና ዘንባባው አይታይም እና

ቅዱስ አጽሟ ባረፈበት ሥነ መቃብር

ሥዕል ለ.

800px-Tombstone_of_Saint_Hripsime

http://en.wikipedia.org/wiki/File:Tombstone_of_Saint_Hripsime.jpg ጽዋውና ዘንባባው አይታይም፡፡  

  • የምስራቅ ባይዛንታየን አብያተክርስቲያናት

በምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ቅድስት አርሴማን ከሣሉባቸው መንገዶች መካከል ተሸፋፍና እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ነው፡፡

ሥዕል ሀ.httpimages.oca.orgiconslgSeptember0930.Rhipsime.jpg

(http://images.oca.org/icons/lg/september/0930.rhipsime.jpg ከላይ የተጠቀሱት 3ቱ ምልክቶች አይታዩም፡፡)

እና ከቅዱስ ጎርጎርዮስ ከሣቴ ብርሃን (የአርመን ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አባት) እና ቅድስት ጋይና (St. Gayane) አብራ ተሥላ ትታያለች

ሥዕል ለ.httpimages.oca.orgiconslgSeptember0930gregory-Rhipsime-gaiana.jpg

http://images.oca.org/icons/lg/september/0930gregoryofarmenia.jpg ጽዋውና ዘንባባው አይታይም፡፡

በሚቀጥለው ጽሑፍ ቅድስት አርሴማ ተብለው የተጠቀሱት ቅዱሳት አንስት አጠር ያለ ታሪካቸውን አቅርባለው ፡፡

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን፡፡ © ከኃይለማርያም ሽመልስ ግንቦት 2007 ዓ.ም.

4 thoughts on “ቅድስት አርሴማ፡ ትክክለኛው የቤትርስቲያን ሥዕሏ የቱ ነው? ክፍል ሁለት

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s