የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል በደብረ ምጥማቅ


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

እንኳን ለእመቤታችን ወርኃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ በዚህ በግንቦት ወር ከሚከበሩ የቤተክርስቲያን ዓበይት መንፈሳዊ በዓልት መካከል እመቤታችን በምድር ግብጽ በደብረ ምጥማቅ የፈጸመችው ታላቅ ተአምር ነው፡፡

በዛሬው ዕለትም ይዤላችሁ የቀረብኩት ጽሑፍም ይህንን ታላቅ በዓል የሚዘክር ጥንታዊ ሥዕል ለእናንተ ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህ ሥዕል የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ሲሆን በሁለተኛው የጎንደር የአሣሣል ዘይቤ (በ18ኛው መ.ክ.ዘ.) የተሣለ ድንቅ የገበታ (በባለ ሦስት ተካፋች Triptych)ላይ ሥዕል ነው፡፡ ሥዕሉም በዓይነቱ ልዩና ብርቅዬ ሲሆን ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ እመቤታችን በዚህ የአሣሣል ጭብጥ ወይም ድርሰት በስፋት ተሥላ ስለማትታይ ነው፡፡

ሥዕሉን ለመመልከት ይህንን ይጫኑ

Saint Virgin Mary at Dabra Metmaq circa 18C. PANEL painting

የሥዕሉ ጭብጥም እመቤታችን ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ለአምስት ቀናት በምትገለጽበት ወቅት የተደረገውን ተአምር ደስታና መንፈሣዊ መስተጋበር በወቅቱ በሕይወት በነበሩ ምእመናን የቤተክርስቲያን ሊቃውንት እና በአፀደ ነፍስ በሚገኙ ቅዱሳን እና መላእክት ያሳያል፡፡

የሥዕሉ መካከለኛው ክፍል ላይ እመቤታችን በመላእክት ተከባና በክብር ተቀምጣ ይታያል፡፡ ከሌሎቹም ገጸባሕርያ በአካል ገዘፍ ተደርጋ ተሥላ የሚታይ ሲሆን፤ ይህ ደግሞ ከቤተክርስቲያን የአሣሣል ትውፊት አንዱ የሆነውን ዋና የሥዕሉ ባለቤት አግዝፎ እና በሥዕሉ መሀል ላይ አድርጎ መሣል ያጠይቃል፡፡

የሥዕሉ የግራና ቀኝ ገጽ የላይኛው ክፍል ላይ ደግሞ ካህናትና ደናግላን እመቤታችንን በከበሮ በጸናጽል ሲያመሰግኗት ይታያል፡፡ በታችኛው የግራ ክፍል መላእክት ሲሰግዱ፤ በታችኛው የቀኝ ክፍል ደግሞ ፈረሰኛ ሰማእታት ሲሰግዱ ይታያል፡፡

በአጠቃላይ ተአምረ ማርያም የተባለው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ሁኔታውን እንዲህ በማለት በደብረ ምጥማቅ እንዴት እመቤታችን ለሕዝበ ክርስቲያኑእንዴት እንደምትታይ እንዲህ በማለት ይገልጸዋል ‹‹የምትገለጸውም ብቻዋን አይደለም ክንፍ ያላቸው መላእክት ይገለጻሉ አንጂ፤ ዳግመኛም በፈረስ የተቀመጡ መንፈሳውያን የሚሆኑ ክርስቲያን ሰማዕታት ይመጣሉ። መጥተውም ከፈርሳቸው ወርደው ማርያም ለሚሏት ከእግሯ በታች ወድቀው ይሰግዳሉ።››

የወላዲተ አምላክ በረከቷ አማለጅነቷ ዘወትር ከቤተክርስቲያን መሪዎች ሊቃነ ጳጳሳት፣ ኤጲስ ቆጶሳት፣ ቀሳውስት፣ ዳያቆናት አንባቢያን፣ መዘምራን፣ ሠዓሊያን፣ ወንዶችም ሴቶችም አይለየን፡፡

ይህ ጽሑፍ በግንቦት ወር በዕለተ ፳፩/21፣ በ፳፻፯/2007 ዓ.ም. በኃይለማርያም ተጻፈ፡፡
ምንጭ፡- ተአምረ ማርያም፤ግእዝና ፡አማርኛ።ገጽ፡60-61።

© ከኃይለማርያም ሽመልስ ግንቦት 2007 ዓ.ም.

2 thoughts on “የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል በደብረ ምጥማቅ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s