ቅድስት አርሴማ፡ ትክክለኛው የቤትርስቲያን ሥዕሏ የቱ ነው? ክፍል 1


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ውድ አንባቢያን ለዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት ወቅታዊና አሳዛኝ ስለሆነ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ነው፡፡ ይኸውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሥዕሎችን ይመለከታል፡፡ ቤተክርስቲያናችን ስንዱ እመቤት በመሆኗ መንፈሳዊ ምስጢርን፣ ታሪክንና ትውፊትን በማስተባበር ልዩና እንደ እንቁ የሚያበራ ሥርዓትን ሠርታለች፡፡ ሆኖም ግን ከእውቀት ማነስ የተነሣ ሥርዓቶቿ እየተጣሱ ይገኛሉ፡፡ ይህንን እንዲቆምና ወደ ትክክለኛው የቤክርስቲያን ትውፊት ምእመናን እንዲመለሱ ተከታታይ ትምህርቶችን በቅዱሳት ሥዕላት ዙርያ አዘጋጅቻለሁ መልካም ንባብ፡፡ click for pdf

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ

 • በቅድስት አርሴማ ሥዕል ዙርያ ስለሚታዩ ብዥታዎችን ለማጥራትና

መግቢያ

ቅድስት አርሴማ ማን ናት?

እናታችን ቅድስት አርሴማ እግዚአብሔርን በቅንነት ያገለገሉ ከነበሩት ካህናት ወገን የሆነ ፣ ቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ከቅድስት አትናስያ በስእለት ተወለደች። ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ብሉይን ከአዲስ ተምራ እያነበበች እንዲሁም በተግባር እየተረጎመች ዘወትር በጸሎት ትተጋ ነበር: ትውልዷ ሮም ቢሆንም በሰማዕትነት ያረፈችው በአርመን ነው፡፡ እኛ አርሴማ ስንላት እነርሱ Saint Hripsime ይሏታል፡፡ የዚህች ወጣት ሰማዕት ታሪክ በስንክሳር በመስከረም 29 ቀን ተጽፏል፡፡ ታሪኳን የበለጠ ለማወቅ ገድሏን አሊያም ይህንን ተጭኖ ያንብ(http://en.wikipedia.org/wiki/Rhipsime)፡፡[1]

የቅድስት አርሴማ ሥዕሏ የትኛው ነው?

በሀገራችን ያሉ ክርስቲያኖች ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ያላቸውን ትልቅ ፍቅር በመመልከት አንዳንድ ሰዎች የተለያዩ ቅዱሳት አንስትን በእርሷ ስም ሥዕሉን ለብቻው አሊያም የገጽ ሽፋን በማድረግ በውስጥ ገድሏን ወይም አጭር የሕይወት ታሪኳን በማካተት ይሸጣሉ። ከዚህ በተጨማሪም በመረጃ መረብና ማኅበራዊ ድረገጾች ሰማዕቷን የሚዘክሩ ሥዕሎችም በዚህ የተሳሳተ መረጃ ሰለባ የሰማዕቷን ትክክለኛ ያልሆነ ሥዕል ሲጠቀሙ ይታያል።

እነኚህን ሥዕላት ለመጠቀማቸው ምክንያታቸው ደግሞ ለቅድስት አርሴማ የተሰጣትን ፀጋ ይኸውም

 • ጽዋ [ማንኛውም ሰማዕት የሰማዕትነቱን ጽዋ (የሞትን ጽዋ) መቀበሉን ያመለክታል ማቴ 26፡39]፣
 • ዘንባባ ዝንጣፊ [የድል፣ የሰማያዊት ኢየሩሳሌም እና የሕይወት ምልክት] እና
 • መስቀል [መከራውን ያሸነፉበት ኃይል ምልክት] መሠረት በማድረግ ነው።

ሆኖም ግን በሥዕሎቿ ላይ የሚገኙት እነኚህ ምልክቶች የቅድስት አርሴማ ብቻ ሳይሆኑ የሌሎች ቅዱሳት አንስትም ጭምር ናቸው እንጂ። ለምሳሌ ለመጥቀስ ያህል

  • ቅድስት በርብራ፣ ቅድስት ማሪና ዘአንጾኪያ፣ ቅድስት ኢየሉጣና ልጇ ቅዱስ ቂርቆስ፣ ቅድስት ድሚያ፣ ቅድስት ሙሕራኤል እና ሌሎችም ተጠቃሽ ናቸው።[2]

ነገር ግን ቅድስት አርሴማ ተብለው ተሰራጭተው ከሚሸጡት አሊያም በየድረገጹ[3] ሰማዕቷን ከሚዘክሩ ሥዕሎች በአብዛኛው በሚያስብል መልኩ የእርሷ ሥዕሎች አይደሉም፡፡ በመሆኑም ከሥር ቅድስት አርሴማ ተብለው የሚገለጹ ሥዕሎች አንድ በአንድ የማን ሥዕል እንደሆኑ እንመልከት፡፡

 • ቅድስት በርበራ (Saint Barbara)

ሀገራችን ውስጥ በብዛት ከሚሰራጩት የቅድስት አርሴማ ተብለው ከሚሸጡ ሥዕላት መካከል የቅድስት በርብራ ሥዕላት ከፍተኛው ሥፍራ ይይዛል። ከቅድስት በርብራ ሥዕሎችም ውስጥ ሁለት ሥዕሎቿ ቅድስት አርሴማ ተብለው እየተሸጡ ይገኛሉ፡፡ ሥዕሎቹን ከሥር ይመልከቷቸው፡፡ ሁለቱን ሥዕሎችን በማስተዋል ብንመለከታቸው በጽርእ ቋንቋ «Η ΑΓΙΑ ΒΑΡΒΑΡΑ» የሚል ፊደልን እንመለከታል ይህ ደግሞ ቅድስት በርብራ ወይም SAINT BARBARA በእንግሊዘኛው ይሆናል፡፡

 • ቅድስት ሉሲያ (Saint Lucia)

ከቅድስት በርብራ በመቀጠል በስፋት የቅድስት አርሴማ እየተባለ የሚሰራጨው ሥዕል የቅድስት ሉሲያ ነው፡፡

 • ቅድስት ኪይሪያኬ (Η ΑΓΙΑ KYPIAKH Saint Kyriake)
 • ቅድስት ካትሪን ዘአሌክሳንድርያ (Η ΑΓΙΑ AIKATEPINH Saint Catherine)
ቅድስት ካትሪን ዘአሌክሳንድርያ (Η ΑΓΙΑ AIKATEPINH Saint Catherine)
ቅድስት ካትሪን ዘአሌክሳንድርያ (Η ΑΓΙΑ AIKATEPINH Saint Catherine)
 • እንደ ቅድስት በርብራም በስፋት ባይታዩም የቅድስት አርሴማ ተብለው ከሚሸጡት ሥዕላት መካከል የቅድስት ካትሪንና የቅድስት ኪይሪያኬ ሁለቱ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ አላጋጠሙኝም እንጂ ሌሎችም ቅዱሳን ሊኖሩ እንደሚችሉ ግምቴ ነው።

የኢትዮጵያውያን ሠዓሊያን ቅድስት አርሴማን ሥለዋት ያውቃሉ?

ቅድስት አርሴማ ሥዕል st Arsema Circa 17 Century Ethiopian panel painting Icon
ቅድስት አርሴማ ሥዕል Circa 17 Century

በተለያዩ ጊዜያት ከላይ የተገለጸውን እውነታ ለሰዎች ለማስረዳት ስሞከር የገጠመኝ ፈተና «እነኚህ ሥዕላት የቅድስት አርሴማ ካልሆነ ኢትዮጵያውያን ቅድስት አርሴማን ከዚህ በፊት ሥለዋት ያውቃሉ?» የሚለው ጥያቄ ነበር። ለዚህ ጥያቄ መለስ የሚሆነኝን መረጃ ያገኘሁት ደግሞ ከመቐለ ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው ኮኽሎ የሐንስ ተብላ በምትጠራው ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው ጥንታዊ የብራና «ገድለ ሰማዕታት» የተሰኘ መጽሐፍ ላይ ነበር። ይህ አስደናቂ መጽሐፍ ሲሆን በውስጡ የመላእክትን ሥዕላት እንዲሁም የብዙ ሰማዕታት ሥዕላትን እንዲሁም በተለያዩ መንገድ የተሠሩ ሐረጋት የያዘ ገድል ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በጥንታዊው የአሣሣል ዘይቤ ቅድስት አርሴማ ተሥላ ትገኛለች። የዚህ መጽሐፍን ዕድሜ በእርግጠኛነት መረጃው የሌለኝ ቢሆንም ከአሣሣል ዘይቤው በመነሣት ግን በ15ኛው መ.ክ.ዘ. የነበረውን የአሣሣል ዘይቤ የያዘ ይመስላል።

ከዚህ በተጨማሪ በመጀመሪያው የጎንደር አሣሣል ዘይቤ የተሳለ የገበታ ሥዕል ላይ የቅድስት አርሴማ ሥዕል በስስ ቅጂ ለማግኘት ችያለሁ፡፡ ሆኖም ግን የዚህ ሥዕል የሚገኝበት ቦታና መቼ እንደተሠራ መረጃው እስከአሁን የለኝም፤ ይሁን እንጂ ከአሣሣል ዘይቤው በመነሳት ሥዕሉ በ17ኛው መ.ክ.ዘ. እንደተሠራ መገመት ይቻላል፡፡

በዘመናችንም ኦርቶዶክሳዊ ትውፊትንና ገደሏን መሠረት በማድረግ የተሠራ ሥዕል በአ.አ. ቦሌ ሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን በሴቶች መግቢያ በር ላይ ማየት ትችላላችሁ፡፡ በማኀበረ ቅዱሳን ንዋየ ቅዱሳት መሸጫ መደብርም (አምስትኪሎ ቅርንጫፍ ሕንጻው ላይ) ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

ማጠቃለያ

ጌታችን በወንጌሉ እውነትን እውነት፤ ሐሰትን ሐሰት ብለን እንድንናገር ያስተምረናል፡፡ በመሆኑም እውነተኛውን የቅድስት አርሴማን ወካይ የሆነውን ሥዕሏን እንድንጠቀም ለማሳሰብ እፈልጋለሁ፡፡ ከዚያም ሲቀጥል በሥዕሉ ላይ የተወከሉት ሌሎች ስለክርስቶስ ሲሉ ሰማእትነት የተቀበሉትን ቅዱሳንን እንድናከብር ያስፈልጋል፡፡

(የዚህ ቀጣይ ክፍል የቅድስት አርሴማ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት እንዴት እንደሣሏት  እና ቅድስት አርሴማ ተብለው የተጠቀሱት ቅዱሳት አንስት አጠር ያለ መግለጫ ከአሣሣል መለያዎቻቸው ጋር አቀርባለሁ)

ይቀጥላል . . .


© ከኃይለማርያም ሽመልስ ግንቦት 2007 ዓ.ም.

ምንጭ

1. http://www.danielkibret.com/2014/10/blog-post_8.html http://arsemakidist.blogspot.com/2011/07/blog-post.html

2. መምህር እንግዳ መርጊያ። የኒቆሞዲያዋ ኮከብ ሰማዕት ቅድስት በርብራ። 39-40።

3. http://stteklehaimanotottawa.org/sunday-school/teaching

7 thoughts on “ቅድስት አርሴማ፡ ትክክለኛው የቤትርስቲያን ሥዕሏ የቱ ነው? ክፍል 1

 1. Good job….it would have been better to post a picture of the painting you saw at Semit Kidus Giorgis church with their permission so people would have other options and recommend for painters to come up with similar.

  Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s