የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ለቅድስት አፎምያ ተአምር ሲያደርግ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ለቅድስት አፎምያ ተአምር ሲያደርግ

በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ለቅድስት አፎምያ የተደረገ ተአምር


ቅድስት አፎምያ የተባለች ሴት አንድ እግዚአብሔርን የሚፈራ አስተራኒቆስ የተባለ ሰው ሚስት ናት ይህም ሰው ምጽዋትን የሚሰጥ ሦስት በዓላትን በየወሩ የሚያከብር ነበረ ፤ እሊኽውም በዓላት የመላእክት አለቃ የሚሆን የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ወር በገባ በየዓሥራ ሁለት ቀን የእመቤታችን ቅድሰት ድንግል ማርያምን በየወሩ በ21 ቀን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደቱን መታሰቢያ በዓል ወር በባተ በ29 ቀን ሲያከብርና መታሰቢያቸውንም ሲያደርግ ይኖር ነበር።

ይህም ሰው የሚሞትበት ቀን በደረሰ ጊዜ በሕይወቱ ሳለ የሚያደርገውን ምፅዋት እንዳታሰቀር አዘዛት ይልቁንም የእሊህን የሦስቱን መታሰቢያ በዓላት ዝክር እንዳታስታጉል አደራ አላት። እሷም በቤቷ ውስጥ አኑራ ከሰይጣን ፈተና ትከላከልበት ዘንደ የሚካኤልን ሥዕል አሠርቶ እንዲሠጣት ባሏን ጠየቀችውና አሠርቶ ሰጣት።ባሏም ከዚህ ዓለም በሞት በተለየ ጊዜ አስቀድሞ እሱ ከሚያደርገው በጎ ስራ አንዳችም ሳታጓድል ትሠራ ጀመረ።

ሰይጣን ቅድስት አፎሚያን ሊያሳስት ሲሞክርና በሥዕለ ቅዱስ ሚካኤል ስታሸንፈውሰይጣን ቅድስት አፎሚያን ሊያሳስት ሲሞክርና በሥዕለ ቅዱስ ሚካኤል ስታሸንፈው(18-19ኛውመ.ክ.ዘ?)
ሰይጣን ቅድስት አፎሚያን ሊያሳስት ሲሞክርና በሥዕለ ቅዱስ ሚካኤል ስታሸንፈው

 

ሰይጣን ይህንን በተመለከተ ጊዜ በቅንዓት ተነሣባት በመበልተ መነኮሳዩት ተመስሎ እየመጣ ስላንቺ በጣም ነው የማዝነው እያለ በነገሩ ሊያግባባት ሞከረ። ቀጥሎም ባልሽ እንደሆነ መንግስተ ሰማያትን ወርሷል ምፅዋትን አይፈልግም ባላት ጊዜ እሷም ከእንግዲህ ከሌላ ወንድ ጋር ላልገናኝ ለእግዚአብሐር የመሐላ ቃሌን ሰጥቻለሁና አላደርግውም ስትል መለሰችለት። ርግቦችና ቁራዎች ሰንኳ ባላቸው ከሞተ ሌላ ባል አያውቁም በአርያ እግዚአብሔር ለተፈጠሩ ሰዎችማ ይህን ማድረግ እንዴት ይገባል አለችው። ነገሩን እንዳልተቀበለችው ባየ ጊዜ መልኩን ለውጦ ዛሬ ባይቻለኝ በሌላ ቀን መጥቼ ሃሳቤን እንድትቀበይ አደርጋለሁ ሲል በታላቅ ቃል ጮኸ። እሷም የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አወጣችና ከዚያ ድምጥማጡን አጠፋችው

ከዚያም በሰኔ 12 ቀን እንደልማዷ ለማክበር ስትዘጋጅ ሣለ ዳግመኛ ያ ሰይጣን በመልአክ አምሳል ተመስሎ መጣና ሰላም ላንቺ ይሁን ቸር አለሽ? እኔ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ እነሆ ገንዘብሽን በምፅዋት ማባከንሽን ትተሽ ከምዕመናን ወገን ለአንዱ ሚስት ትሆኝ ዘንድ እግዚአብሔር ወደ አንቺ ልኮኛል። በዚህም ላይ ያለ ባል የምትኖር ሴት መቅዘፊያ የሌላት ወይም መልሕቋ አንደተቆረጠ መርከብ መሆኗን እወቂ አላት። ከመጽሐፈ ብሉያት ልዩ ልዩ ጥቅሶችን እያመጣ ተመልከች አብርሃም ይስሐቅና ያዕቆብ ዳዊት ሌሎችም እነሱን የመሰሉ ሁሉ ሚስት አግብተዋል ነገር ግን የእግዚአብሔር ባለሟሎች እንደነበሩ አስቢ አላት።

ቅድስት አፎምያም መልሳ አንተ የእግዚአብሔር መላእክ ከሆንክ የመታወቂያ ምልክት የሚሆን ትእምርተ መስቀል ወዴት አለ የንጉሥ መልእክተኛ የሆነ ሁሉ የንጉሡን ማኅተም ሳይዝ ወደ ሌላው መልእክት ሊያደርስ አይሄድምና አለችው። ሰይጣንም ይህንን በሰማ ጊዜ መልኩ ተለወጠ ዘሎም አነቃት።

ቅዱስ ሚካኤል በመስቀሉ ሰይጣንን ጥሎ ሲያሸንፈው (20ኛውመ.ክ.ዘ.)
ቅዱስ ሚካኤል በመስቀሉ ሰይጣንን ጥሎ ሲያሸንፈው

በዚህም ጊዜ አፎምያ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ድረስልኝ እያለች ስትጮህ ፈጥኖ ደረሰና አዳናት። ሰይጣኑንም በብዙ አይነት ሥቃይ ካሠቃየው በኋላ እግዚአብሔር እስከ ዓለም ፍጻሜ ድርስ ታግሶኛልና ይቅር በለኝ አታጥፋኝ ብሎ ስለለመነው ተወው።

ቅዱስ ሚካኤልም ቅድስት አፎምያን ሂደሽ ቤትሽን አዘጋጂ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ትለያለሽና፤ እነሆ እግዚአብሔርም ዓይን ያላየውን ጆሮ ያለሰማውን ልቡና ያላሰበውን ዋጋሽን አዘጋጅቶልሻል ብሎ ከነገራት በኋላ ሰላምታ ሰጥቷት ወደ ሰማይ ዐረገ። ከዚያም ለበዓሉ የሚያስፈልገውን ከአዘጋጀች በኋላ ወደ ኤጲስ ቆጶሱና ካህናቱ ዘንድ መልእክተኛ ላከችና መጡ ቀጥሎም በእነሱ እጅ ለነዳያንና ችግረኞች ምፅዋት ይሰጡላት ዘንድ ገንዘብ ሰጠቻቸው። ከዚህም በኋላ የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል በደረቷና በፊቷ ላይ አድርጋ ወደ እግዚአብሔር እየጸለየች የቅዱስ ሚካኤል በሚከበርበት ዕለት በሰኔ ዓሥራ ሁለት ቀን በክብር ዓረፈች።[1]


ምንጭ

1. የሰኔ ድርሳነ ሚካኤል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s